Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ነህምያ 9:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም እንደ ሰማይ ከዋ​ክ​ብት አበ​ዛህ፤ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ወደ ተና​ገ​ር​ህ​ላ​ቸው ምድር አገ​ባ​ሃ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 ወንዶች ልጆቻቸውን እንደ ሰማይ ከዋክብት አበዛሃቸው፤ አባቶቻቸው ገብተው እንዲወርሱ ወዳዘዝሃቸውም ምድር አገባሃቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 ልጆቻቸውን እንደ ሰማይ ከዋክብት አበዛህ፥ እንዲገቡና እንዲወርሷት ለአባቶቻቸው ወደ ነገርሃቸው ምድር አገባሃቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 ብዛታቸው እንደ ሰማይ ከዋክብት የሆኑ ልጆችን ሰጠሃቸው፥ ለቀድሞ አባቶቻቸው ትሰጣቸው ዘንድ ቃል የገባህላቸውን ምድር፥ በድል አድራጊነት እንዲይዙ ፈቀድክላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 ልጆቻቸውንም እንደ ሰማይ ከዋክብት አበዛህ፥ ይገቡና ይወርሱ ዘንድ ለአባቶቻቸው ወደ ተናገርህላቸውም ምድር አገባሃቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ነህምያ 9:23
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለአ​ብ​ራም ተገ​ለ​ጠ​ለ​ትና፥ “ይህ​ችን ምድር ለዘ​ርህ እሰ​ጣ​ለሁ” አለው። አብ​ራ​ምም ለእ​ርሱ ለተ​ገ​ለ​ጠ​ለት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚያ መሠ​ው​ያን ሠራ።


በዚ​ያ​ችም ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ብ​ራም ተስፋ ያደ​ረ​ገ​ለ​ትን ቃል ኪዳን አጸና፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “ከግ​ብፅ ወንዝ ጀምሮ እስከ ትልቁ ወንዝ እስከ ኤፍ​ራ​ጥስ ወንዝ ድረስ ይህ​ችን ምድር ለዘ​ርህ እሰ​ጣ​ታ​ለሁ፤


ወደ ሜዳም አወ​ጣ​ውና “ወደ ላይ ወደ ሰማይ ተመ​ል​ከት፤ ልት​ቈ​ጥ​ራ​ቸው ትችል እን​ደ​ሆነ ከዋ​ክ​ብ​ትን ቍጠ​ራ​ቸው። ዘር​ህም እን​ደ​ዚሁ ነው” አለው።


በው​ስ​ጥዋ የም​ት​ኖ​ር​ባ​ትን ይህ​ችን ምድር፥ የከ​ነ​ዓ​ንን ምድር ሁሉ፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይገ​ዙ​አት ዘንድ ለዘ​ርህ እሰ​ጣ​ለሁ፤ አም​ላ​ክም እሆ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ።”


ዘር​ህ​ንም እንደ ሰማይ ከዋ​ክ​ብ​ትና በባ​ሕር ዳር እን​ዳለ አሸዋ ፈጽሞ አበ​ዛ​ዋ​ለሁ፤ ዘር​ህም የጠ​ላት ሀገ​ሮ​ችን ይወ​ር​ሳሉ፤


በዚ​ህች ምድር ተቀ​መጥ፤ ከአ​ንተ ጋርም እሆ​ና​ለሁ፤ እባ​ር​ክ​ሃ​ለ​ሁም፤ ይህ​ችን ምድር ሁሉ ለአ​ን​ተም፥ ለዘ​ር​ህም እሰ​ጣ​ለ​ሁና፥ ለአ​ባ​ት​ህም ለአ​ብ​ር​ሃም የማ​ል​ሁ​ለ​ትን መሐላ ከአ​ንተ ጋር አጸ​ና​ለሁ።


ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝቡ እስ​ራ​ኤ​ልን እንደ ሰማይ ከዋ​ክ​ብት ያበዛ ዘንድ ተና​ግሮ ነበ​ርና ዳዊት ከሃያ ዓመት በታች የነ​በ​ሩ​ትን አል​ቈ​ጠ​ረም።


ነገር ግን እን​ዳ​ስ​ጨ​ነ​ቁ​አ​ቸው መጠን እን​ዲሁ በዙ፤ እጅ​ግም ጸኑ ፤ ግብ​ፃ​ው​ያ​ንም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ይጸ​የ​ፉ​አ​ቸው ነበር።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በዙ፤ ተባ​ዙም፤ የተ​ጠ​ሉም ሆኑ። እጅ​ግም ጸኑ፤ ምድ​ሪ​ቱም በእ​ነ​ርሱ ሞላች።


የአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል አል​ሰ​ማ​ች​ሁ​ምና ከብ​ዛ​ታ​ችሁ የተ​ነሣ እንደ ሰማይ ከዋ​ክ​ብት የነ​በ​ረው ቍጥ​ራ​ችሁ ጥቂት ሆኖ ይቀ​ራል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች