የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዮናስ 1:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በባ​ሕሩ ላይ ታላቅ ነፋ​ስን አመጣ፤ በባ​ሕ​ሩም ላይ ታላቅ ማዕ​በል ሆነ፤ መር​ከ​ቢ​ቱም ልት​ሰ​በር ቀረ​በች።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እግዚአብሔርም በባሕሩ ላይ ታላቅ ነፋስን ላከ፤ ከባድ ማዕበልም ተነሥቶ መርከቢቱን አንገላታት፤ ልትሰበርም ተቃረበች።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ጌታ ግን በባሕሩ ላይ ታላቅ ነፋስን አስነሣ፥ በባሕሩም ላይ ታላቅ ማዕበል ተነሣ፥ መርከቢቱም ልትሰበር ቀረበች።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እግዚአብሔር ግን በባሕሩ ላይ ከባድ ነፋስን አስነሣ፤ በባሕሩም ላይ የተቀሰቀሰው ማዕበል ብርቱ ከመሆኑ የተነሣ መርከቢቱ ልትሰበር ተቃረበች፤

ምዕራፉን ተመልከት



ዮናስ 1:4
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ምድ​ርን በውኃ ላይ ያጸና፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤


ብቻ​ውን ታላ​ላቅ ብር​ሃ​ና​ትን የሠራ፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤


እሳ​ትና በረዶ፥ አመ​ዳ​ይና ውርጭ፥ ቃሉን የሚ​ያ​ደ​ርግ ዐውሎ ነፋ​ስም፤


ሙሴም በት​ሩን ወደ ሰማይ ዘረጋ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የደ​ቡ​ብን ነፋስ ያን ቀን ሁሉ ሌሊ​ቱ​ንም ሁሉ አመጣ፤ ማለ​ዳም በሆነ ጊዜ የደ​ቡብ ነፋስ አን​በ​ጣን አመጣ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከባ​ሕር ዐውሎ ነፋ​ሱን አስ​ወ​ገደ፤ አን​በ​ጣ​ዎ​ች​ንም ወስዶ በኤ​ር​ትራ ባሕር ውስጥ ጣላ​ቸው፤ አንድ አን​በ​ጣም እን​ኳን በግ​ብፅ ዳርቻ ሁሉ አል​ቀ​ረም።


ሙሴም በባ​ሕሩ ላይ እጁን ዘረጋ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሌሊ​ቱን ሁሉ ጽኑ የአ​ዜብ ነፋስ አም​ጥቶ ባሕ​ሩን አስ​ወ​ገ​ደው፤ ባሕ​ሩ​ንም አደ​ረ​ቀው፤ ውኃ​ውም ተከ​ፈለ።


ነፋ​ስ​ህን ላክህ፤ ባሕ​ርም ከደ​ና​ቸው፤ በብዙ ውኆች ውስጥ እንደ አረር ሰጠሙ።


ድም​ፁን ባሰማ ጊዜ ውኆች በሰ​ማይ ይታ​ወ​ካሉ፤ ከም​ድ​ርም ዳር ደመ​ና​ትን ያወ​ጣል፤ ለዝ​ና​ብም ጊዜ መብ​ረ​ቅን ያደ​ር​ጋል፤ ነፋ​ስ​ንም ከቤተ መዛ​ግ​ብቱ ያወ​ጣል።


እነሆ ነጐ​ድ​ጓ​ድን የሚ​ያ​ጸና፥ ነፋ​ስ​ንም የፈ​ጠረ፥ የመ​ሢ​ሕን ነገር ለሰው የሚ​ነ​ግር፥ ንጋ​ትን ጭጋግ የሚ​ያ​ደ​ርግ፥ በም​ድ​ርም ከፍ​ታ​ዎች ላይ የሚ​ረ​ግጥ፥ ስሙ ሁሉን የሚ​ችል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እኔ ነኝ።”


ነፋ​ስም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ወጣ፤ ከባ​ሕ​ርም ድር​ጭ​ቶ​ችን አወጣ፤ የአ​ንድ ቀንም መን​ገድ ያህል በዚህ፥ የአ​ንድ ቀንም መን​ገድ ያህል በዚያ በሰ​ፈሩ ላይ በተ​ና​ቸው፤ በዚ​ያም በሰ​ፈሩ ዙሪያ ከፍ​ታው ከም​ድር ወደ ላይ ሁለት ክንድ ነበረ።