የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዮሐንስ 11:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ቀኑ ዐሥራ ሁለት ሰዓት አይ​ደ​ለ​ምን? በቀን የሚ​ሄድ አይ​ሰ​ና​ከ​ልም፤ የዚ​ህን ዓለም ብር​ሃን ያያ​ልና።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ቀኑ ዐሥራ ሁለት ሰዓት ብርሃን አይደለምን? ከዚህ ዓለም ብርሃን የተነሣ ስለሚያይ በቀን የሚመላለስ አይሰናከልም፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ኢየሱስም መልሶ “በቀን ውስጥ ዐሥራ ሁለት ሰዓት ይገኙ የለምን? በቀን የሚመላለስ የዚህን ዓለም ብርሃን ያያልና አይሰናከልም፤

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “በቀን ውስጥ ያለው ጊዜ ዐሥራ ሁለት ሰዓት አይደለምን? በቀን የሚመላለስ የዚህን ዓለም ብርሃን ስለሚያይ አይሰናከልም።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ኢየሱስም መልሶ፦ “ቀኑ አሥራ ሁለት ሰዓት አይደለምን? በቀን የሚመላለስ ቢኖር የዚህን ዓለም ብርሃን ያያልና አይሰናከልም፤

ምዕራፉን ተመልከት



ዮሐንስ 11:9
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በመንገድህም ሁሉ በመተማመን ትሄዳለህ፥ እግሮችህም አይሰነካከሉም።


እያ​ለ​ቀሱ ሄዱ፤ እኔም በማ​ጽ​ና​ናት አመ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በወ​ንዝ ዳር በቅን መን​ገድ አስ​ሄ​ዳ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በእ​ር​ሱም አይ​ሰ​ና​ከ​ሉም፤ እኔ ለእ​ስ​ራ​ኤል አባት ነኝና፥ ኤፍ​ሬ​ምም በኵሬ ነውና።”


በሌ​ሊት የሚ​ሄድ ግን ይሰ​ነ​ካ​ከ​ላል፤ በው​ስጡ የሚ​ያ​የው ብር​ሃን የለ​ምና።”


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ ገና ለጥ​ቂት ጊዜ ብር​ሃን ከእ​ና​ንተ ጋር ነው፤ በጨ​ለማ የሚ​መ​ላ​ለስ የሚ​ሄ​ድ​በ​ትን አያ​ው​ቅ​ምና ጨለማ እን​ዳ​ያ​ገ​ኛ​ችሁ ብር​ሃን ሳለ​ላ​ችሁ ተመ​ላ​ለሱ፤


ነገር ግን ቀን ሳለ የላ​ከ​ኝን ሥራ ልሠራ ይገ​ባ​ኛል፤ ማንም ሥራ ሊሠራ የማ​ይ​ች​ል​ባት ሌሊት ትመ​ጣ​ለ​ችና።


ወንድሙንም የሚወድ በብርሃን ይኖራል ማሰናከያም የለበትም፤