የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ኤርምያስ 7:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

መን​ገ​ዳ​ች​ሁ​ንና ሥራ​ች​ሁን ፈጽ​ማ​ችሁ ብታ​ቃኑ፥ በሰ​ውና በጓ​ደ​ኛው መካ​ከል ቅን ፍርድ ብት​ፈ​ርዱ፤

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

መንገዳችሁንና ሥራችሁን በርግጥ ብታሳምሩ፣ በመካከላችሁ ቅንነት ቢኖር፣

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

መንገዳችሁንና ሥራችሁን ፈጽማችሁ ብታሳምሩ፥ በሰውና በጎረቤቱ መካከል ቅን ፍርድ ብትፈርዱ፥

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

“ይልቅስ የአኗኗራችሁንና የተግባራችሁን ሁኔታ ለውጡ፤ እርስ በርሳችሁ ቅንነት በሞላበት ፍቅር ተሳስራችሁ ኑሩ፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

መንገዳችሁንና ሥራችሁን ፈጽማችሁ ብታሳምሩ፥ በሰውና በጎረቤቱ መካከል ቅን ፍርድ ብትፈርዱ፥

ምዕራፉን ተመልከት



ኤርምያስ 7:5
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እሽ ብት​ሉና ብት​ሰ​ሙኝ የም​ድ​ርን በረ​ከት ትበ​ላ​ላ​ችሁ፤


አር​ኖ​ንም በም​ት​ኖ​ር​በት ምሽግ መጠ​ለ​ያን ትሠራ ዘንድ ብዙ ትመ​ክ​ራ​ለች፤ በቀ​ትር ጊዜ እንደ ሌሊት ደን​ግ​ጠው ይሸ​ሻሉ፤ ወደ እና​ን​ተም አታ​ስ​ገ​ቡ​አ​ቸው።


የዳ​ዊት ቤት ሆይ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ስለ ሥራ​ችሁ ክፋት ቍጣዬ እንደ እሳት እን​ዳ​ይ​ነ​ድ​ድና ማንም ሳያ​ጠ​ፋው እን​ዳ​ያ​ቃ​ጥል፥ በማ​ለዳ ፍር​ድን አድ​ርጉ፤ የተ​ነ​ጠ​ቀ​ው​ንም ከአ​ስ​ጨ​ና​ቂው እጅ አድኑ።


በአ​ባ​ትህ ዝግባ አዳ​ራሽ ስለ ሠራህ በውኑ ትነ​ግ​ሣ​ለ​ህን? በውኑ አባ​ትህ አይ​በ​ላና አይ​ጠ​ጣም ነበ​ርን? ፍር​ድ​ንና ጽድ​ቅ​ንስ አያ​ደ​ር​ግም ነበ​ርን? በዚ​ያም ጊዜ መል​ካም ሆኖ​ለት ነበር።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ፍር​ድ​ንና ጽድ​ቅን አድ​ርጉ፤ የተ​ነ​ጠ​ቀ​ው​ንም ከአ​ስ​ጨ​ና​ቂው እጅ አድኑ፤ መጻ​ተ​ኛ​ው​ንና ድሃ​አ​ደ​ጉን፥ ባል​ቴ​ቲ​ቱ​ንም አት​በ​ድሉ፤ አታ​ም​ፁ​ባ​ቸ​ውም፤ በዚ​ህም ስፍራ ንጹሕ ደምን አታ​ፍ​ስሱ።


አሁ​ንም መን​ገ​ዳ​ች​ሁ​ንና ሥራ​ች​ሁን አሳ​ምሩ፤ የአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁ​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የተ​ና​ገ​ረ​ባ​ች​ሁን ክፉ ነገር ይተ​ዋል።


የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ መን​ገ​ዳ​ች​ሁ​ንና ሥራ​ች​ሁን አቅኑ፤ በዚ​ህም ስፍራ አሳ​ድ​ራ​ች​ኋ​ለሁ።


እጁ​ንም ከዐ​መፅ ቢመ​ልስ፥ አራ​ጣ​ንም አት​ርፎ ባይ​ወ​ስድ፥ ፍር​ዴ​ንም ቢያ​ደ​ርግ፥ በት​እ​ዛ​ዜም ቢሄድ፥ እርሱ ፈጽሞ በሕ​ይ​ወት ይኖ​ራል እንጂ በአ​ባቱ ኀጢ​አት አይ​ሞ​ትም።


“ሰውም ጻድቅ ቢሆን ፍር​ድ​ንና ቅን ነገ​ር​ንም ቢያ​ደ​ርግ፤


በአ​ራጣ ባያ​በ​ድር፥ አት​ር​ፎም ባይ​ወ​ስድ፥ እጁ​ንም ከኀ​ጢ​አት ቢመ​ልስ፥ በሰ​ውና በሰው መካ​ከ​ልም የእ​ው​ነ​ትን ፍርድ ቢፈ​ርድ፥


እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝና ሰው ባል​ን​ጀ​ራ​ውን አያ​ስ​ጨ​ንቅ፤ ነገር ግን አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፍራ።


ኢየሩሳሌምና በዙሪያዋ ያሉ ከተሞች ገና ሰዎች ባሉባቸው ጊዜ፥ በምቾትም ተቀምጠው ሳሉ፥ ደቡቡና ቈላውም ሰዎች ባሉባቸው ጊዜ፥ እግዚአብሔር በቀደሙት ነቢያት እጅ የተናገረውን ቃል መስማት አይገባችሁምን?


በኢ​ያ​ቢስ ገለ​ዓድ በሚ​ኖሩ መካ​ከ​ልም ወንድ ያላ​ወቁ አራት መቶ ቆነ​ጃ​ጅት ደና​ግ​ልን አገኙ፤ በከ​ነ​ዓ​ንም ሀገር ወዳ​ለ​ችው ወደ ሴሎ ወደ ሰፈሩ አመ​ጡ​አ​ቸው።


በዚ​ያ​ችም ቀን ዲቦ​ራና የአ​ቢኒ​ሔም ልጅ ባርቅ እን​ዲህ ብለው ዘመሩ፦