የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ የባቢሎንን ንጉሥ በቅጥርም ውጭ የከበቡአችሁን ከለዳውያንን የምትወጉበትን በእጃችሁ ያለውን የጦር መሣሪያችሁን እሰጣችኋለሁ፤ እነዚያንም በዚህች ከተማ መካከል እሰበስባቸዋለሁ።
ኤርምያስ 38:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “በዚች ከተማ የሚቀመጥ በሰይፍና በራብ፥ በቸነፈርም ይሞታል፤ ወደ ከለዳውያን የሚወጣ ግን በሕይወት ይኖራል፤ ነፍሱም እንደ ምርኮ ትሆንለታለች፤ በሕይወትም ይኖራል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘በዚህች ከተማ የሚቀር ሁሉ በሰይፍ፣ በራብ ወይም በቸነፈር ይሞታል፤ ይህን ስፍራ ለቅቆ ወደ ባቢሎናውያን የሚሄድ ሁሉ ይተርፋል፤ ያመልጣል፤ በሕይወትም ይኖራል።’ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኤርምያስ እንዲህ ብሏልና፦ “ጌታ እንዲህ ይላል፦ በዚህች ከተማ የሚቀመጥ በሰይፍና በራብ በቸነፈርም ይሞታል፤ ወደ ከለዳውያን ግን የሚወጣ በሕይወት ይኖራል፥ እርሱም በምርኮ ነፍሱን ያድናል፥ በሕይወትም ይኖራል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የተናገርኩትም ቃል ይህ ነበር፦ “በከተማይቱ የሚቀሩ ሁሉ በጦርነት፥ በረሀብ ወይም በወረርሽኝ ይሞታሉ፤ ወደ ባቢሎናውያን ሄዶ እጁን የሚሰጥ ግን አይገደልም፤ እርሱ ሕይወቱን ለማትረፍ ያመልጣል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኤርምያስ እንዲህ ብሎአልና፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በዚህች ከተማ የሚቀመጥ በሰይፍና በራብ በቸነፈርም ይሞታል፥ ወደ ከለዳውያን ግን የሚወጣ በሕይወት ይኖራል፥ ነፍሱም እንደ ምርኮ ትሆንለታለች፥ በሕይወትም ይኖራል። |
የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ የባቢሎንን ንጉሥ በቅጥርም ውጭ የከበቡአችሁን ከለዳውያንን የምትወጉበትን በእጃችሁ ያለውን የጦር መሣሪያችሁን እሰጣችኋለሁ፤ እነዚያንም በዚህች ከተማ መካከል እሰበስባቸዋለሁ።
እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል፥ “ከክፋቱ የተነሣ ይበላ ዘንድ እንደማይቻል እንደ ክፉው በለስ፥ እንዲሁ የይሁዳን ንጉሥ ሴዴቅያስን፤ አለቆቹንም፥ በዚች ሀገር የሚቀሩትንም የኢየሩሳሌምን ቅሬታ፥ በግብጽም ሀገር የሚቀመጡትን እንዲሁ አደርጋቸዋለሁ።
ነገር ግን ከባቢሎን ንጉሥ ቀንበር በታች አንገቱን ዝቅ የሚያደርገውንና የሚገዛለትን ሕዝብ በሀገሩ ላይ እተወዋለሁ፤ እርሱም ያርሳታል፤ ይቀመጥባትማል።”
ለባቢሎን ንጉሥ ይገዛ ዘንድ እንቢ ስላለ ሕዝብ እግዚአብሔር እንደ ተናገረ፥ አንተና ሕዝብህ በሰይፍና በራብ፥ በቸነፈርም ለምን ትሞታላችሁ?
እግዚአብሔር በዳዊት ዙፋን ስለ ተቀመጠ ንጉሥ፥ ከእናንተም ጋር ስላልተማረኩት ወንድሞቻችሁ፥ በዚህች ከተማ ስለሚኖሩ ሕዝብ ሁሉ እንዲህ ይላልና፦
በሰይፍና በራብ፥ በቸነፈርም አሳድዳቸዋለሁ፤ ባሳደድሁባቸውም አሕዛብ ሁሉ ዘንድ ለርግማንና ለጥፋት፥ ለማፍዋጫም፥ ለመሰደቢያም እንዲሆኑ በምድር መንግሥታት ሁሉ ዘንድ ለመበተን አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ።
ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ሰው ሁሉ ለወንድሙና ለባልንጀራው ዓመተ ኅድገትን ለማድረግ እኔን አልሰማችሁም፤ እነሆ እኔ ለሰይፍና ለቸነፈር፥ ለራብም ዓመተ ኅድገትን አውጅባችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ በምድርም መንግሥታት ሁሉ መካከል እበትናችኋለሁ።
ፈጽሜ አድንሃለሁ፤ ሰውነትህም እንደ ምርኮ ትሆንልሃለች እንጂ በሰይፍ አትወድቅም፤ በእኔ ታምነሃልና፥” ይላል እግዚአብሔር።
ወደ ግብፅም ይገቡ ዘንድ፥ በዚያም ይቀመጡ ዘንድ ፊታቸውን በሚያቀኑ ሰዎች ሁሉ እንዲህ ይሆንባቸዋል፤ በሰይፍና በራብ፥ በቸነፈርም ያልቃሉ፤ እኔም ከማመጣባቸው ክፉ ነገር ማንም አይቀርም፤ ማንም አያመልጥም።
አሁንም ሄዳችሁ እንድትቀመጡ በወደዳችሁበት ስፍራ በሰይፍና በራብ፥ በቸነፈርም እንድትሞቱ በእርግጥ ዕወቁ።”
ኢየሩሳሌምንም በመዐት እንደ ጐበኘሁ፥ እንዲሁ በግብፅ ምድር የሚኖሩትን በሰይፍና በራብ በቸነፈርም እጐበኛለሁ።
ለራስህ ታላላቅ ነገሮችን ትፈልጋለህን? በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ እነሆ ክፉ ነገርን አመጣለሁና አትፈልጋቸው፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ነገር ግን በሄድህበት ስፍራ ሁሉ ነፍስህን እንደ ምርኮ አድርጌ እሰጥሃለሁ።”
ጌታ እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል፥ “ይልቁንስ ሰውንና እንስሳን ከእርስዋ አጠፋ ዘንድ በኢየሩሳሌም ላይ አራቱን ክፉ መቅሠፍቶችን፥ ሰይፍንና ራብን፥ ክፉዎችንም አውሬዎች፥ ቸነፈርንም ስሰድድባት፥
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በእጅህ አጨብጭብ፤ በእግርህም አሸብሽብ፤ ስለ እስራኤል ቤት ርኵሰት ሁሉ ወዮ ወዮ በል፤ በረኀብና በጦር፥ በቸነፈርም ይጠፋሉ።