Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 39:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ፈጽሜ አድ​ን​ሃ​ለሁ፤ ሰው​ነ​ት​ህም እንደ ምርኮ ትሆ​ን​ል​ሃ​ለች እንጂ በሰ​ይፍ አት​ወ​ድ​ቅም፤ በእኔ ታም​ነ​ሃ​ልና፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 እታደግሃለሁ፤ በእኔ ታምነሃልና በሕይወት ታመልጣለህ እንጂ በሰይፍ አትወድቅም፤ ይላል እግዚአብሔር።’ ”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ፈጽሜ አድንሃለሁ፥ ነፍስህም ለአንተ በምርኮ ትድናለች እንጂ በሰይፍ አንተ አትወድቅም፥ በእኔ ታምነሃልና፥ ይላል ጌታ።’ ”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 እኔ በሰላም ስለምጠብቅህ አትሞትም፤ በእኔ ስለ ታመንክ በሕይወት ትተርፋለህ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ፈጽሜ አድንሃለሁ ነፍስህም እንደ ምርኮ ትሆንልሃለች እንጂ በሰይፍ አትወድቅም፥ በእኔ ታምነሃልና፥ ይላል እግዚአብሔር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 39:18
19 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በሚ​ዋ​ጉ​በ​ትም ጊዜ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኸ​ዋ​ልና በእ​ር​ሱም ታም​ነ​ዋ​ልና አዳ​ና​ቸው፤ በላ​ያ​ቸ​ውም በረ​ቱ​ባ​ቸው፥ አጋ​ራ​ው​ያ​ንና ከእ​ነ​ርሱ ጋር የነ​በ​ሩ​ትም ሁሉ በእ​ጃ​ቸው ተሰጡ።


በራብ ጊዜ ከሞት ያድ​ን​ሃል፥ በጦ​ር​ነ​ትም ጊዜ ከሰ​ይፍ እጅ ያድ​ን​ሃል።


ጥበ​ብን አጽ​ኑ​አት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ይ​ቈጣ፥ እና​ን​ተም ከጽ​ድቅ መን​ገድ እን​ዳ​ት​ጠፉ፥ ቍጣው ፈጥና በነ​ደ​ደች ጊዜ፥ በእ​ርሱ የታ​መኑ ሁሉ ብፁ​ዓን ናቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በል​ባ​ቸው የዋ​ሃን ለሆኑ ቅርብ ነው፥ በመ​ን​ፈስ ትሑ​ታን የሆ​ኑ​ት​ንም ያድ​ና​ቸ​ዋል።


አቤቱ፥ አንተ እይ፥ ዝምም አት​በል፤ አቤቱ፥ ከእኔ አት​ራቅ።


ከቍ​ጣህ ፊት የተ​ነሣ ለሥ​ጋዬ ድኅ​ነት የለ​ውም፤ ከኀ​ጢ​አ​ቴም ፊት የተ​ነሣ ለአ​ጥ​ን​ቶቼ ሰላም የላ​ቸ​ውም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ምሕ​ረ​ቱን ይሰ​ጣል፥ ምድ​ርም ፍሬ​ዋን ትሰ​ጣ​ለች።


ኃጥ​ኣን እንደ ሣር በበ​ቀሉ ጊዜ፥ ዐመ​ፃን የሚ​ያ​ደ​ር​ጉም ሁሉ በለ​መ​ለሙ ጊዜ፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ዓለም እን​ደ​ሚ​ጠፉ ነው።


በአ​ንተ ላይ ታም​ና​ለ​ችና በአ​ንተ የም​ት​ደ​ገፍ ነፍ​ስን ፈጽ​መህ በሰ​ላም ትጠ​ብ​ቃ​ታ​ለህ።


በዚ​ህች ከተማ ውስጥ የሚ​ቀ​መጥ በሰ​ይ​ፍና በራብ፥ በቸ​ነ​ፈ​ርም ይሞ​ታል፤ ወጥቶ ወደ ከበ​ቡ​አ​ችሁ ወደ ከለ​ዳ​ው​ያን የሚ​ገባ ግን በሕ​ይ​ወት ይኖ​ራል፤ ሰው​ነ​ቱም ምርኮ ትሆ​ና​ለች።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “በዚች ከተማ የሚ​ቀ​መጥ በሰ​ይ​ፍና በራብ፥ በቸ​ነ​ፈ​ርም ይሞ​ታል፤ ወደ ከለ​ዳ​ው​ያን የሚ​ወጣ ግን በሕ​ይ​ወት ይኖ​ራል፤ ነፍ​ሱም እንደ ምርኮ ትሆ​ን​ለ​ታ​ለች፤ በሕ​ይ​ወ​ትም ይኖ​ራል።


ከሕግ ወጥ​ተው የበ​ደሉ በሕግ ይፈ​ረ​ድ​ባ​ቸ​ዋል፤ ያለ ሕግ የበ​ደሉ ሁሉም ያለ ሕግ ይፈ​ረ​ድ​ባ​ቸ​ዋል።


ይኸ​ውም አስ​ቀ​ድ​መን በክ​ር​ስ​ቶስ ኢየ​ሱስ ተስፋ ያደ​ረ​ግን እኛ ለክ​ብሩ ምስ​ጋና እን​ሆን ዘንድ ነው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች