የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ኤርምያስ 18:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ከጭ​ቃም ይሠ​ራው የነ​በ​ረው ዕቃ ከሸ​ክላ ሠሪው እጅ ወደቀ፤ ሸክላ ሠሪ​ውም እንደ ወደደ ዳግ​መኛ ሌላ ዕቃ አድ​ርጎ ሠራው።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከጭቃ ይሠራው የነበረውም ሸክላ በእጁ ላይ ተበላሸ፤ ሸክላ ሠሪውም በሚፈልገው ሌላ ቅርጽ መልሶ አበጀው።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከጭቃም ይሠራው የነበረ ዕቃ በሸክላ ሠሪው እጅ ተበላሸ፥ ሸክላ ሠሪውም እንደ ወደደ መልሶ ሌላ ዕቃ አድርጎ ሠራው።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የሸክላውም ዕቃ በእጁ ላይ በሚበላሽበት ጊዜ እንደገና ለውሶ በሚፈልገው ዐይነት ሌላ ዕቃ አድርጎ ይሠራው ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ከጭቃም ይሠራው የነበረ ዕቃ በሸክላ ሠሪው እጅ ተበላሸ፥ ሸክላ ሠሪውም እንደ ወደደ መልሶ ሌላ ዕቃ አድርጎ ሠራው።

ምዕራፉን ተመልከት



ኤርምያስ 18:4
5 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“እንደ ሸክላ ሠሪ ሥራ ውብ አድ​ርጌ ሠራ​ሁህ፤ ምድ​ርን የሚ​ያ​ርስ ሁል​ጊዜ ያር​ሳ​ልን? ጭቃ ሠሪ​ውን፦ ምን ትሠ​ራ​ለህ? እጅ የለ​ህ​ምና መሥ​ራት አት​ች​ልም ይለ​ዋ​ልን? ጭቃ ሠሪ​ውን ይከ​ራ​ከ​ረ​ዋ​ልን?


ወደ ሸክላ ሠሪ​ውም ቤት ወረ​ድሁ፤ እነ​ሆም ሥራ​ውን በዓ​ለት ላይ ሲሠራ አገ​ኘ​ሁት።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ።


“የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! ይህ ሸክላ ሠሪ እን​ደ​ሚ​ሠራ በውኑ እኔ በእ​ና​ንተ ዘንድ መሥ​ራት አይ​ቻ​ለ​ኝ​ምን? እነሆ ጭቃው በሸ​ክላ ሠሪ እጅ እን​ዳለ፥ እን​ዲሁ እና​ንተ በእኔ እጅ አላ​ችሁ።