Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 18:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ከጭቃም ይሠራው የነበረ ዕቃ በሸክላ ሠሪው እጅ ተበላሸ፥ ሸክላ ሠሪውም እንደ ወደደ መልሶ ሌላ ዕቃ አድርጎ ሠራው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ከጭቃ ይሠራው የነበረውም ሸክላ በእጁ ላይ ተበላሸ፤ ሸክላ ሠሪውም በሚፈልገው ሌላ ቅርጽ መልሶ አበጀው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 የሸክላውም ዕቃ በእጁ ላይ በሚበላሽበት ጊዜ እንደገና ለውሶ በሚፈልገው ዐይነት ሌላ ዕቃ አድርጎ ይሠራው ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ከጭ​ቃም ይሠ​ራው የነ​በ​ረው ዕቃ ከሸ​ክላ ሠሪው እጅ ወደቀ፤ ሸክላ ሠሪ​ውም እንደ ወደደ ዳግ​መኛ ሌላ ዕቃ አድ​ርጎ ሠራው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ከጭቃም ይሠራው የነበረ ዕቃ በሸክላ ሠሪው እጅ ተበላሸ፥ ሸክላ ሠሪውም እንደ ወደደ መልሶ ሌላ ዕቃ አድርጎ ሠራው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 18:4
5 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከሠሪው ጋር ለሚታገል ወዮለት! በምድር ሸክላዎች መካከል ያለ ሸክላ ነው። ጭቃ ሠሪውን፦ ምን ትሠራለህ? ወይስ ሥራህ እጅ የለውም ይላልን?


ወደ ሸክላ ሠሪው ቤትም ወረድሁ፥ እነሆም፥ ሥራውን በመንኰራኵር ላይ ይሠራ ነበር።


የጌታም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ።


“የእስራኤል ቤት ሆይ! ይህ ሸክላ ሠሪ እንደሚሠራ በውኑ እኔ በእናንተ ላይ መሥራት አልችልምን? ይላል ጌታ፤ እነሆ፥ ጭቃው በሸክላ ሠሪ እጅ እንዳለ፥ የእስራኤል ቤት ሆይ! እንዲሁ እናንተ በእኔ እጅ አላችሁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች