የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘፍጥረት 5:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አዳ​ምም ሁለት መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፤ ልጅ​ንም እንደ ምሳ​ሌው እንደ መልኩ ወለደ፤ ስሙ​ንም ሴት ብሎ ጠራው።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አዳም፣ ዕድሜው 130 ዓመት በሆነ ጊዜ፣ እርሱን ራሱን የሚመስል ወንድ ልጅ ወለደ፤ ስሙንም ሴት ብሎ ጠራው።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አዳምም መቶ ሠላሳ ዓመት ሲኖር፥ እሱን የሚመስል፥ አምሳያው የሆነ፥ የልጅ አባት ሆነ፤ ሤት ብሎም ስም አወጣለት።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አዳም መቶ ሠላሳ ዓመት በሆነው ጊዜ በመልኩና በአምሳያው እርሱን የሚመስል ወንድ ልጅ ወለደ፤ “ሤት” የሚል ስምም አወጣለት።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አዳምም ሁለት መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፤ ልጅንም በምሳሌው እንደ መልኩ ወለደ ስሙንም ሴት ብሎ ጠራው።

ምዕራፉን ተመልከት



ዘፍጥረት 5:3
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አዳ​ምም ዳግ​መኛ ሚስ​ቱን ዐወ​ቃት፤ ፀነ​ሰ​ችም፤ ወንድ ልጅ​ንም ወለ​ደች። ስሙ​ንም ቃየል በገ​ደ​ለው በአ​ቤል ፈንታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሌላ ዘር ተክ​ቶ​ል​ኛል ስትል ሴት አለ​ችው።


ወን​ድና ሴት አድ​ርጎ ፈጠ​ራ​ቸው፤ ባረ​ካ​ቸ​ውም። እነ​ር​ሱ​ንም በፈ​ጠ​ረ​በት ቀን ስሙን አዳም ብሎ ጠራው።


አዳ​ምም ሴትን ከወ​ለደ በኋላ የኖ​ረው ሰባት መቶ ዓመት ሆነ፤ ወን​ዶ​ች​ንም፥ ሴቶ​ች​ንም ወለደ።


ከር​ኵ​ሰት የሚ​ነጻ ማን ነው? አንድ ስንኳ የለም።


ጻድቅ ሰው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እን​ዴት ንጹሕ ይሆ​ናል? ከሴ​ትስ የተ​ወ​ለደ ራሱን ንጹሕ ማድ​ረግ እን​ዴት ይች​ላል?


ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለዘ​ለ​ዓ​ለም ያፈ​ር​ስ​ሃል፤ ከቤ​ት​ህም ይነ​ቅ​ል​ሃል፥ ያፈ​ል​ስ​ሃ​ልም፥ ሥር​ህ​ንም ከሕ​ያ​ዋን ምድር።


መል​አ​ኩም መልሶ እን​ዲህ አላት፥ “መን​ፈስ ቅዱስ ያድ​ር​ብ​ሻል፤ የል​ዑል ኀይ​ልም ይጋ​ር​ድ​ሻል፤ ከአ​ንቺ የሚ​ወ​ለ​ደ​ውም ቅዱስ ነው፤ የል​ዑል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅም ይባ​ላል።


የቃ​ይ​ናን ልጅ፥ የአ​ር​ፋ​ክ​ስድ ልጅ፥ የሴም ልጅ፥ የኖኅ ልጅ፥ የላ​ሜሕ ልጅ፥


ከሥጋ የተ​ወ​ለደ ሥጋ ነውና፤ ከመ​ን​ፈ​ስም የተ​ወ​ለደ መን​ፈስ ነውና።


ስለ​ዚ​ህም በአ​ንድ ሰው በደል ምክ​ን​ያት ኀጢ​አት ወደ ዓለም ገባች፤ ስለ​ዚ​ችም ኀጢ​አት ሞት ገባ፤ እን​ደ​ዚ​ሁም ሁሉ ኀጢ​አ​ትን ስለ አደ​ረጉ በሰው ሁሉ ላይ ሞት መጣ።


የፍ​ጥ​ረቱ ሁሉ አካል አንድ አይ​ደ​ለ​ምና፤ የሰው አካል ሌላ ነው፤ የእ​ን​ስ​ሳም አካል ሌላ ነው፤ የወፍ አካ​ልም ሌላ ነው፤ የዓሣ አካ​ልም ሌላ ነው።


የመ​ሬ​ታ​ዊ​ውን መልክ እንደ ለበ​ስን እን​ዲሁ የሰ​ማ​ያ​ዊ​ውን መልክ ደግሞ እን​ለ​ብ​ሳ​ለን።


እኛ ሁላ​ችን ቀድሞ እንደ ሥጋ​ችን ምኞት ኖርን፤ የሥ​ጋ​ች​ን​ንም ፈቃ​ድና ያሰ​ብ​ነ​ውን አደ​ረ​ግን፤ እንደ ሌሎች ኃጥ​አ​ንም ሁሉ የጥ​ፋት ልጆች ሆንን።