የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘፍጥረት 45:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ቃሉ​ንም ከፍ አድ​ርጎ አለ​ቀሰ፤ የግ​ብፅ ሰዎ​ችም ሰሙ፤ በፈ​ር​ዖን ቤትም ተሰማ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ዮሴፍም ድምፁን ከፍ አድርጎ በማልቀሱ፣ ግብጻውያን ሰሙት፤ ወሬውም ወደ ፈርዖን ቤተ ሰዎች ደረሰ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ድምፁንም ከፍ አድርጎ አለቀሰ፥ የግብጽ ሰዎችም ሰሙ፥ በፈርዖን ቤትም ተሰማ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በዚህ ጊዜ ግብጻውያን እስኪሰሙት ድረስ ድምፁን ከፍ አድርጎ አለቀሰ፤ የፈርዖንም ቤተሰብ ወሬውን ሰማ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ቃሉንም ከፍ አድርጎ አልቀሰ የግብፅ ሰዎችም ሰሙ በፈርዖን ቤትም ተሰማ።

ምዕራፉን ተመልከት



ዘፍጥረት 45:2
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዮሴ​ፍም ከእ​ነ​ርሱ ዘወር ብሎ አለ​ቀሰ፤ ደግ​ሞም ወደ እነ​ርሱ ተመ​ልሶ ተና​ገ​ራ​ቸው፤ ስም​ዖ​ን​ንም ከእ​ነ​ርሱ ለይቶ ወስዶ በፊ​ታ​ቸው አሰ​ረው።


ዮሴ​ፍም ታወከ፤ አን​ጀቱ ወን​ድ​ሙን ናፍ​ቆ​ታ​ልና፤ ሊያ​ለ​ቅ​ስም ወደደ፤ ወደ እል​ፍ​ኙም ገብቶ በዚያ አለ​ቀሰ።


የወ​ን​ድ​ሙን የብ​ን​ያ​ም​ንም አን​ገት አቅፎ አለ​ቀሰ፤ ብን​ያ​ምም በአ​ን​ገቱ ላይ አለ​ቀሰ።


ወን​ድ​ሞ​ቹን ሁሉ ሳማ​ቸው፤ በእ​ነ​ር​ሱም ላይ አለ​ቀሰ፤ ከዚ​ያም በኋላ ወን​ድ​ሞቹ ከእ​ርሱ ጋር ተጨ​ዋ​ወቱ።


ዮሴ​ፍም ሰረ​ገ​ላ​ውን አዘ​ጋጀ፤ አባ​ቱ​ንም እስ​ራ​ኤ​ልን ሊገ​ና​ኘው ወደ ኤሮስ ከተማ ወጣ፤ በአ​የ​ውም ጊዜ አን​ገ​ቱን አቀ​ፈው፤ ረዥም ጊዜም አለ​ቀሰ።


“አቤቱ፥ በፊ​ትህ በእ​ው​ነ​ትና በፍ​ጹም ልብ እንደ ሄድሁ፥ መል​ካም ነገ​ርም እን​ዳ​ደ​ረ​ግሁ አስብ።” ሕዝ​ቅ​ያ​ስም እጅግ አለ​ቀሰ።


በዳዊትም ቤት ላይ፥ በኢየሩሳሌምም በሚኖሩት ላይ፥ የሞገስንና የልመናን መንፈስ አፈስሳለሁ፣ ወደ እርሱም ወደ ወጉት ይመለከታሉ፣ ሰውም ለአንድያ ልጁ እንደሚያለቅስ ያለቅሱለታል፥ ሰውም ለበኵር ልጁ እንደሚያዝን በመራራ ኅዘን ያዝኑለታል።


ማኅ​በ​ሩም ሁሉ ድም​ፃ​ቸ​ውን አን​ስ​ተው ጮኹ፤ ሕዝ​ቡም ሌሊ​ቱን ሁሉ አለ​ቀሱ።


ሁሉም እጅግ አለ​ቀሱ፤ ጳው​ሎ​ስ​ንም አን​ገ​ቱን አቅ​ፈው ሳሙት።


እግዚአብሔር በየባላችሁ ቤት ዕረፍት ይስጣችሁ አለቻቸው። ሳመቻቸውም፣ ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው አለቀሱ።