የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘፍጥረት 40:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በጌ​ታው ቤት ከእ​ርሱ ጋር በግ​ዞት የነ​በ​ሩ​ት​ንም የፈ​ር​ዖን ሹሞች እን​ዲህ ብሎ ጠየ​ቃ​ቸው፥ “እና​ንት ዛሬ ስለ​ምን አዝ​ና​ች​ኋል?”

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ስለዚህም፣ “ምነው ዛሬስ ፊታችሁ ላይ ሐዘን ይነበባል?” በማለት ዐብረውት በጌታው ግቢ የታሰሩትን የፈርዖን ሹማምት ጠየቃቸው።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ስለዚህም፥ “ምነው ዛሬስ ፊታችሁ ላይ ኀዘን ይነበባል?” በማለት አብረውት በጌታው ግቢ የታሰሩትን የፈርዖን ሹማምንት ጠየቃቸው።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

“ዛሬ በፊታችሁ ላይ ሐዘን የሚታየው ለምንድን ነው?” አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በጌታው ቤት ከእርሱ ጋር በግዞት የነበሩትንም የፈርዖንን ሹማምት እንዲህ ብሎ ጠየቃቸው፦ እናንተ ዛሬ ስለ ምን አዝናችኍል?

ምዕራፉን ተመልከት



ዘፍጥረት 40:7
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዮሴ​ፍም ማልዶ ወደ እነ​ርሱ ገባ፤ እነ​ሆም፥ አዝ​ነው አያ​ቸው።


ሦስት ቀን ያህ​ልም በግ​ዞት ቤት ጨመ​ራ​ቸው።


እር​ሱም፥ “የን​ጉሥ ልጅ ሆይ፥ ስለ​ምን በየ​ቀኑ እን​ዲህ ከሳህ? አት​ነ​ግ​ረ​ኝ​ምን?” አለው። አም​ኖ​ንም፥ “የወ​ን​ድ​ሜን የአ​ቤ​ሴ​ሎ​ምን እኅት ትዕ​ማ​ርን እወ​ድ​ዳ​ታ​ለሁ” አለው።


ንጉ​ሡም፥ “ሳት​ታ​መም ፊትህ ለምን አዘነ? ይህ የልብ ኀዘን ነው እንጂ ሌላ አይ​ደ​ለም” አለኝ። እጅ​ግም ብዙ አድ​ርጌ ፈራሁ።


ጌታ​ች​ንም፥ “በት​ካዜ እየ​ሄ​ዳ​ችሁ እርስ በር​ሳ​ችሁ የም​ት​ነ​ጋ​ገ​ሩት ይህ ነገር ምን​ድን ነው?” አላ​ቸው።


እር​ሱም፥ “የሠ​ራ​ኋ​ቸ​ውን አማ​ል​ክ​ቴን፥ ካህ​ኑ​ንም ይዛ​ችሁ ሄዳ​ች​ኋል፤ ለእኔ ምን ተዋ​ች​ሁ​ልኝ? እና​ን​ተስ፦ ለምን ትጮ​ኻ​ለህ እን​ዴት ትሉ​ኛ​ላ​ችሁ?” አለ።


ባልዋ ሕል​ቃ​ናም፥ “ሐና ሆይ!” አላት እር​ስ​ዋም፥ “ጌታዬ እነ​ሆኝ” አለ​ችው። እር​ሱም፥ “ለምን ታለ​ቅ​ሻ​ለሽ? ለም​ንስ አት​በ​ዪም? ለም​ንስ ልብሽ ያዝ​ን​ብ​ሻል? እኔስ ከዐ​ሥር ልጆች አል​ሻ​ል​ሽ​ምን?” አላት።