የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘፍጥረት 28:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አም​ላኬ ከአ​ንተ ጋር ይሂድ፤ ከፍ ከፍም ያድ​ር​ግህ፤ ይባ​ር​ክህ፤ ያብ​ዛህ፤ ብዙ ሕዝ​ብም ሁን ፤

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሁሉን ቻይ አምላክ ይባርክህ፤ ብዙ ሕዝብ እስክትሆን ድረስ ልጆች አፍራ፤ ዘርህን ያብዛው።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሁሉን የሚችል አምላክም ለብዙ ሕዝብ ጉባኤ እንድትሆን ይባርክህ፥ ያፍራህ፥ ያብዛህ፥

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሁሉን የሚችል እግዚአብሔር ይባርክህ! ብዙ ልጆችም ይስጥህ! የብዙ ሕዝቦችም አባት ያድርግህ!

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሁሉን የሚችል አምላክም ለብዙ ሕዝብ ጉባኤ እንድትሆን ይባርክህ፥

ምዕራፉን ተመልከት



ዘፍጥረት 28:3
23 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ባረ​ካ​ቸው፤ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “ብዙ፤ ተባዙ፤ ምድ​ር​ንም ሙሉ​አት፤ ግዙ​አ​ትም፤ የባ​ሕ​ርን ዓሣ​ዎ​ች​ንና የም​ድር አራ​ዊ​ትን፥ የሰ​ማይ ወፎ​ች​ንና እን​ስ​ሳ​ት​ንም ሁሉ፥ በም​ድር ላይ የሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀ​ሱ​ት​ንም ሁሉ ግዙ​አ​ቸው።”


ዘር​ህ​ንም እንደ ባሕር አሸዋ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ የባ​ሕር አሸ​ዋን ይቈ​ጥር ዘንድ የሚ​ችል ሰው ቢኖር ዘርህ ደግሞ ይቈ​ጠ​ራል።


ስለ ይስ​ማ​ኤ​ልም እነሆ፥ ሰም​ቼ​ሃ​ለሁ፤ እባ​ር​ከ​ዋ​ለሁ፤ አበ​ዛ​ዋ​ለሁ፤ እጅ​ግም አበ​ዛ​ዋ​ለሁ፤ ዐሥራ ሁለት አለ​ቆ​ች​ንም ይወ​ል​ዳል፤ ታላቅ ሕዝ​ብም አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ።


እኅ​ታ​ቸው ርብ​ቃ​ንም መረ​ቁ​አ​ትና፥ “አንቺ እኅ​ታ​ችን፥ እልፍ አእ​ላ​ፋት ሁኚ፤ ዘር​ሽም የጠ​ላት ሀገ​ሮ​ችን ይው​ረስ” አሉ​አት።


በዚ​ያ​ችም ሌሊት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተገ​ለ​ጠ​ለት፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “እኔ የአ​ባ​ትህ የአ​ብ​ር​ሃም አም​ላክ ነኝ፤ አት​ፍራ፤ እኔ ከአ​ንተ ጋር ነኝና፤ እባ​ር​ክ​ሃ​ለሁ፤ ስለ አባ​ትህ ስለ አብ​ር​ሃም ዘር​ህን አበ​ዛ​ዋ​ለሁ።”


ዘር​ህ​ንም እንደ ሰማይ ከዋ​ክ​ብት አበ​ዛ​ዋ​ለሁ፤ ይህ​ች​ንም ምድር ሁሉ ለዘ​ርህ እሰ​ጣ​ለሁ፤ የም​ድ​ርም ሕዝ​ቦች ሁሉ በዘ​ርህ ይባ​ረ​ካሉ፤


ይስ​ሐ​ቅም እጅግ ደነ​ገጠ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “ያደ​ነ​ውን አደን ወደ እኔ ያመ​ጣው ማን ነው? አንተ ሳት​መ​ጣም ከሁሉ በላሁ፤ ባረ​ክ​ሁ​ትም፤ እር​ሱም የተ​ባ​ረከ ነው።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለው፥ “አም​ላ​ክህ እኔ ነኝ፤ ብዛ፤ ተባ​ዛም፤ ሕዝ​ብና የአ​ሕ​ዛብ ማኅ​በር ከአ​ንተ ይሆ​ናል፤ ነገ​ሥ​ታ​ትም ከጕ​ል​በ​ትህ ይወ​ጣሉ።


የሁ​ለ​ተ​ኛ​ው​ንም ስም ኤፍ​ሬም ብሎ ጠራው፤ እን​ዲህ ሲል፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ከ​ራዬ ሀገር አብ​ዝ​ቶ​ኛ​ልና።”


አም​ላ​ኬም በዚያ ሰው ፊት ሞገ​ስን ይስ​ጣ​ችሁ፤ ያን ወን​ድ​ማ​ች​ሁ​ንና ብን​ያ​ም​ንም ይመ​ል​ስ​ላ​ችሁ፤ እኔም ልጆ​ችን እን​ዳ​ጣሁ አጣሁ።”


ያዕ​ቆብ ዮሴ​ፍን አለው፥ “አም​ላኬ በከ​ነ​ዓን ምድር በሎዛ ተገ​ለ​ጠ​ልኝ፤ ባረ​ከ​ኝም።


እን​ዲ​ህም አለኝ፦ እነሆ፥ አበ​ዛ​ሃ​ለሁ፤ አባ​ዛ​ሃ​ለ​ሁም፤ ለብ​ዙም ሕዝብ ጉባኤ አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ፤ ይህ​ች​ንም ምድር ለአ​ንተ፥ ከአ​ን​ተም በኋላ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ርስት ለዘ​ርህ እሰ​ጣ​ታ​ለሁ።


“የእኔ አም​ላክ ረዳህ፤ ከላይ በሰ​ማይ በረ​ከት፥ ሁሉ በሚ​ገ​ኝ​ባት፥ በም​ድር በረ​ከት፥ በጡ​ትና በማ​ኅ​ፀን በረ​ከት ባረ​ከህ፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኖኅ​ንና ልጆ​ቹን ባረ​ካ​ቸው፤ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “ብዙ፤ ተባዙ፤ ምድ​ር​ንም ሙሉ​አት፤ ግዙ​አ​ትም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈ​ሩት ሁሉ፥ በመ​ን​ገ​ዶ​ቹም የሚ​ሄዱ ብፁ​ዓን ናቸው።


ሚስ​ትህ በቤ​ትህ እል​ፍኝ ውስጥ እን​ደ​ሚ​ያ​ፈራ ወይን ትሆ​ና​ለች፤ ልጆ​ች​ህም በማ​ዕ​ድህ ዙሪያ እንደ አዲስ የወ​ይራ ተክል ይሆ​ናሉ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በዙ፤ ተባ​ዙም፤ የተ​ጠ​ሉም ሆኑ። እጅ​ግም ጸኑ፤ ምድ​ሪ​ቱም በእ​ነ​ርሱ ሞላች።


ለአ​ብ​ር​ሃ​ምም፥ ለይ​ስ​ሐ​ቅም፥ ለያ​ዕ​ቆ​ብም ሁሉን እን​ደ​ሚ​ችል አም​ላክ ተገ​ለ​ጥሁ፤ ነገር ግን ስሜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አል​ታ​ወ​ቀ​ላ​ቸ​ውም ነበር።


አባት እሆ​ና​ች​ኋ​ለሁ፤ እና​ን​ተም ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆች ትሆ​ኑ​ኛ​ላ​ችሁ አለ ሁሉን የሚ​ገዛ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።”


ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክና በጉ መቅደስዋ ናቸውና መቅደስ በእርስዋ ዘንድ አላየሁም።


እነሆም፥ ቦዔዝ ከቤተ ልሔም መጣ፥ አጫጆችንም፦ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን አላቸው። እነርሱም፦ እግዚአብሔር ይባርክህ ብለው መለሱለት።