የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘፍጥረት 17:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እን​ግ​ዲህ ስምህ አብ​ራም አይ​ባ​ልም ‘አብ​ር​ሃም’ ይባ​ላል እንጂ፤ ለብዙ አሕ​ዛብ አባት አድ​ር​ጌ​ሃ​ለ​ሁና።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከእንግዲህ ወዲያ ስምህ አብራም መባሉ ቀርቶ አብርሃም ይሆናል፤ የብዙ ሕዝቦች አባት አድርጌሃለሁና።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከዛሬም ጀምሮ እንግዲህ ስምህ አብራም ተብሎ አይጠራ፥ ነገር ግን ስምህ አብርሃም ይሆናል፥ ለብዙ አሕዛብ አባት አድርጌሃለሁና።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የብዙ ሕዝቦች አባት ስለማደርግህም ከእንግዲህ ወዲህ ስምህ አብራም መሆኑ ቀርቶ አብርሃም ይሆናል።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ከዛሬም ጀምሮ እንግዲህ ስምህ አብራም ተብሎ አይጠራ፥ ነገር ግን ስምህ አብርሃም ይሆናል፤ ለብዙ አሕዛብ አባት አድርጌሃለሁና።

ምዕራፉን ተመልከት



ዘፍጥረት 17:5
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አብ​ር​ሃ​ምን አለው፥ “ሚስ​ትህ ሦራ እን​ግ​ዲህ ሦራ ተብላ አት​ጠ​ራም፤ ስምዋ ‘ሣራ’ ይሆ​ናል እንጂ።


አለ​ውም፥ “ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ስምህ እስ​ራ​ኤል ይባል እንጂ ያዕ​ቆብ አይ​ባል፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርና ከሰው ጋር ታግ​ለህ በር​ት​ተ​ሃ​ልና።”


ያዕ​ቆ​ብም፥ “ስም​ህን ንገ​ረኝ” ብሎ ጠየ​ቀው። እር​ሱም፥ “ስሜን ለምን ትጠ​ይ​ቃ​ለህ? ድንቅ ነውና” አለው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለው፥ “ስምህ ያዕ​ቆብ አይ​ባል፤ ስምህ እስ​ራ​ኤል ይባል እንጂ” ስሙ​ንም እስ​ራ​ኤል ብሎ ጠራው።


ደግ​ሞም በነ​ቢዩ በና​ታን እጅ ልኮ ስሙን ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍቁረ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብሎ ጠራው።


አብ​ር​ሃም የተ​ባ​ለው አብ​ራም።


አንተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ ነህ፤ አብ​ራ​ምን መረ​ጥህ፤ ከዑር ከላ​ው​ዴ​ዎ​ንም አወ​ጣ​ኸው፤ ስሙ​ንም አብ​ር​ሃም አል​ኸው፤


ስማ​ች​ሁ​ንም እኔ ለመ​ረ​ጥ​ኋ​ቸው ሕዝቤ ጥጋብ አድ​ር​ጋ​ችሁ ትተ​ዋ​ላ​ችሁ፤ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያጠ​ፋ​ች​ኋል፤ ባሪ​ያ​ዎች ግን በሐ​ዲስ ስም ይጠ​ራሉ።


በነ​ጋ​ውም ጳስ​ኮር ኤር​ም​ያ​ስን ከአ​ዘ​ቅት ውስጥ አወ​ጣው። ኤር​ም​ያ​ስም እን​ዲህ አለው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም​ህን፦ ዘዋሪ ስደ​ተኛ እንጂ ጳስ​ኮር ብሎ አይ​ጠ​ራ​ህም።


በዘ​መ​ኑም ይሁዳ ይድ​ናል፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ተዘ​ልሎ ይቀ​መ​ጣል፤ ይህም ስም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በነ​ቢ​ያት ኢዮ​ሴ​ዴቅ ብሎ የጠ​ራው ነው።


ምድ​ሪ​ቱን ይሰ​ልሉ ዘንድ ሙሴ የላ​ካ​ቸው ሰዎች ስሞች እነ​ዚህ ናቸው። ሙሴም የነ​ዌን ልጅ አው​ሴን ኢያሱ ብሎ ጠራው።


እር​ሱም መጀ​መ​ሪያ ወን​ድሙ ስም​ዖ​ንን አግ​ኝቶ “በት​ር​ጓ​ሜው ክር​ስ​ቶስ የሚ​ሉት መሲ​ሕን አገ​ኘ​ነው” አለው።


“ለብ​ዙ​ዎች አሕ​ዛብ አባት አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ” ተብሎ እንደ ተጻፈ ሙታ​ንን በሚ​ያ​ስ​ነ​ሣ​ቸው፥ የሌ​ሉ​ት​ንም እንደ አሉ በሚ​ያ​ደ​ር​ጋ​ቸው በአ​መ​ነ​በት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አብ​ር​ሃም የሁ​ላ​ችን አባት ነው።


መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ። ድል ለነሣው ከተሰወረ መና እሰጠዋለሁ፤ ነጭ ድንጋይንም እሰጠዋለሁ፤ በድንጋዩም ላይ ከተቀበለው በቀር አንድ ስንኳ የሚያውቀው የሌለ አዲስ ስም ተጽፎአል።