የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘዳግም 5:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዛሬ በዚህ በሕ​ይ​ወት ካላ​ች​ሁት ከእ​ና​ንተ ከሁ​ላ​ችሁ ጋር እንጂ ከአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ ጋር ይህ​ችን ቃል ኪዳን አላ​ጸ​ናም።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እግዚአብሔር ይህን ቃል ኪዳን የገባውም ከአባቶቻችን ጋራ ሳይሆን፣ ዛሬ እዚህ በሕይወት ከምንገኘው ከእኛ ከሁላችን ጋራ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ጌታ ይህችን ቃል ኪዳን ከአባቶቻችን ጋር ብቻ ሳይሆን ያደረገው ዛሬ በዚህ በሕይወት ካለነው ከእኛ ከሁላችንም ጋር ነው።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ቃል ኪዳን ያደረገውም ከአባቶቻችን ጋር ብቻ ሳይሆን፥ አሁን በሕይወት ካለነውም ከእኛ ሁሉ ጋር ነው።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እግዚአብሔር ዛሬ በዚህ በሕይወት ካለነው ከእኛ ከሁላችን ጋር እንጂ ከአባቶቻችን ጋር ይህችን ቃል ኪዳን አላደረገም።

ምዕራፉን ተመልከት



ዘዳግም 5:3
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ቃል ኪዳ​ኔን ግን በሚ​መ​ጣው ዓመት በዚሁ ጊዜ ሣራ ከም​ት​ወ​ል​ድ​ልህ ከይ​ስ​ሐቅ ጋር አቆ​ማ​ለሁ።”


ቃል ኪዳ​ኔ​ንም በእ​ኔና በአ​ንተ መካ​ከል፥ ከአ​ን​ተም በኋላ በዘ​ርህ መካ​ከል በት​ው​ል​ዳ​ቸው ለዘ​ለ​ዓ​ለም ኪዳን አቆ​ማ​ለሁ፤ ለአ​ን​ተና ከአ​ን​ተም በኋላ ለዘ​ርህ አም​ላክ እሆን ዘንድ።


ከግ​ብፅ ሀገር አወ​ጣ​ቸው ዘንድ እጃ​ቸ​ውን በያ​ዝ​ሁ​በት ቀን ከአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ጋር እንደ ገባ​ሁት ያለ ቃል ኪዳን አይ​ደ​ለም፤ እነ​ርሱ በኪ​ዳኔ አል​ጸ​ኑ​ምና፥ እኔም ቸል አል​ኋ​ቸው፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


“የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ አባ​ቶ​ቻ​ች​ሁን ከባ​ር​ነት ቤት ከግ​ብፅ ሀገር በአ​ወ​ጣ​ኋ​ቸው ቀን ከእ​ነ​ርሱ ጋር እን​ዲህ ስል ቃል ኪዳን አደ​ረ​ግሁ፦


እውነት እላችኋለሁ፥ ብዙዎች ነቢያትና ጻድቃን የምታዩትን ሊያዩ ተመኝተው አላዩም፤ የምትሰሙትንም ሊሰሙ ተመኝተው አልሰሙም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በኮ​ሬብ ካደ​ረ​ገው ቃል ኪዳን ሌላ በሞ​ዓብ ምድር ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ጋር ያደ​ር​ገው ዘንድ ሙሴን ያዘ​ዘው የቃል ኪዳኑ ቃሎች እነ​ዚህ ናቸው።


የም​ታ​ደ​ር​ጉት ሁሉ ይከ​ና​ወ​ን​ላ​ችሁ ዘንድ የዚ​ህን ቃል ኪዳን ቃሎች ታደ​ርጉ ዘንድ ጠብቁ።