የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘዳግም 26:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

“አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ርስት አድ​ርጎ ወደ​ሚ​ሰ​ጥህ ምድር በገ​ባህ ጊዜ፥ በወ​ረ​ስ​ሃ​ትም፥ በኖ​ር​ህ​ባ​ትም ጊዜ፥

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አምላክህ እግዚአብሔር ርስት አድርጎ ወደሚሰጥህ ምድር ስትገባ፣ ስትወርሳትና ስትኖርባት፣

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

“ጌታ እግዚአብሔር ርስት አድርጎ ወደሚሰጥህ ምድር ስትገባ፥ ስትወርሳትና ስትኖርባት፥

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

“እግዚአብሔር አምላክህ እንድትወርሳት ወደሚሰጥህ ምድር ገብተህ በምትወርሳትና ተደላድለህ በምትቀመጥባት ጊዜ፥

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አምላክህ እግዚአብሔር ርስት አድርጎ ወደሚሰጥህ ምድር በገባህም ጊዜ፥ በወረስሃትም በኖርህባትም ጊዜ፥

ምዕራፉን ተመልከት



ዘዳግም 26:1
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ብለህ ንገ​ራ​ቸው፤


“ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ብለህ ንገ​ራ​ቸው፦ ወደ​ም​ሰ​ጣ​ችሁ ወደ መኖ​ሪ​ያ​ችሁ ምድር በገ​ባ​ችሁ ጊዜ፥


“ከአ​ን​ተም ነቢይ ወይም ሕልም አላሚ ቢነሣ፥ ምል​ክ​ትም፥ ተአ​ም​ራ​ትም ቢሰ​ጥህ፥


ነገር ግን ፈጽ​መህ ተና​ገር፤ እር​ሱን ለመ​ግ​ደል በፊት ያንተ እጅ፥ ከዚ​ያም በኋላ የሕ​ዝቡ ሁሉ እጅ በላዩ ትሁን።


“አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ርስት አድ​ርጎ ወደ​ሚ​ሰ​ጥህ ምድር በገ​ባህ፥ በወ​ረ​ስ​ሃ​ትም ጊዜ፥ በተ​ቀ​መ​ጥ​ህ​ባ​ትም ጊዜ፦ በዙ​ሪ​ያዬ እን​ዳ​ሉት አሕ​ዛብ ሁሉ በላዬ አለቃ እሾ​ማ​ለሁ ብትል፥


“አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ​ሚ​ሰ​ጥህ ምድር በገ​ባህ ጊዜ እነ​ዚያ አሕ​ዛብ የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ትን ርኵ​ሰት ታደ​ርግ ዘንድ አት​ማር።


አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትወ​ር​ሳት ዘንድ በሚ​ሰ​ጥህ ምድር ውስጥ ንጹሕ ደም እን​ዳ​ይ​ፈ​ስስ፥ በው​ስ​ጥ​ህም የደም ወን​ጀ​ለኛ እን​ዳ​ይ​ኖር።


ለአ​ን​ተም መን​ገ​ድ​ህን ታዘ​ጋ​ጃ​ለህ፤ አም​ላ​ክ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ያ​ወ​ር​ስ​ህን ምድር ከሦ​ስት አድ​ር​ገህ ትከ​ፍ​ላ​ለህ፤ ለነ​ፍሰ ገዳ​ይም ሁሉ መማ​ጸኛ ይሁን።


ስለ​ዚህ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትወ​ር​ሳት ዘንድ በሚ​ሰ​ጥህ ምድር ከሚ​ከ​ብ​ቡህ ጠላ​ቶ​ችህ ሁሉ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ባሳ​ረ​ፈህ ጊዜ፥ የዐ​ማ​ሌ​ቅን ዝክረ ስሙን ከሰ​ማይ በታች አጥ​ፋው፤ ይህ​ንም አት​ርሳ።


አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሚ​ሰ​ጥህ ምድር ከም​ት​ሰ​በ​ስ​በው ፍሬ ሁሉ ቀዳ​ም​ያት ውሰድ፤ በዕ​ን​ቅ​ብም አድ​ር​ገው፤ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስሙ ይጠ​ራ​በት ዘንድ ወደ መረ​ጠው ስፍራ ይዘህ ሂድ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እና​ንተ በተ​ና​ገ​ራ​ች​ሁት ምክ​ን​ያት ተቈ​ጣኝ፤ ዮር​ዳ​ኖ​ስ​ንም እን​ዳ​ል​ሻ​ገር፥ አም​ላ​ክ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ርስት አድ​ርጎ ወደ​ሚ​ሰ​ጥህ ወደ መል​ካ​ሚቱ ምድር እን​ዳ​ል​ገባ ማለ።


አንተ ግን በዚህ በእኔ ዘንድ ቁም፤ ርስት አድ​ርጌ በም​ሰ​ጣ​ቸው ምድር ላይ ያደ​ር​ጉ​አት ዘንድ የም​ታ​ስ​ተ​ም​ራ​ቸ​ውን ትእ​ዛ​ዜ​ንና ሥር​ዐ​ቴን፥ ፍር​ዴ​ንም ሁሉ እነ​ግ​ር​ሃ​ለሁ።


“አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልት​ወ​ር​ሳት ወደ​ም​ት​ገ​ባ​ባት ምድር ባመ​ጣህ ጊዜ፥ ከፊ​ት​ህም ብዙና ታላ​ላቅ አሕ​ዛ​ብን፥ ከአ​ንተ የበ​ለ​ጡ​ትን፥ የበ​ረ​ቱ​ት​ንም ሰባ​ቱን አሕ​ዛብ፥ ኬጤ​ዎ​ና​ዊ​ውን፥ ጌር​ጌ​ሴ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ከነ​ዓ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ፌር​ዜ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ኤዌ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም ባወጣ ጊዜ፥