ከዚህም በኋላ በሌሊት ራእይ አየሁ፤ እነሆም የምታስፈራና የምታስደነግጥ፥ እጅግም የበረታች፥ ታላላቅም የብረት ጥርሶች የነበሩአት አራተኛ አውሬ ነበረች፤ ትበላና ታደቅቅ ነበር፥ የቀረውንም በእግርዋ ትረግጥ ነበር፤ ከእርስዋም በፊት ከነበሩት አራዊት ሁሉ የተለየች ነበረች፤ ዐሥር ቀንዶችም ነበሩአት።