ከወንዙም ውኃ በላይ የነበረው፥ በፍታም የለበሰው ሰው ቀኝና ግራ እጁን ወደ ሰማይ አንሥቶ፥ “ለዘመንና ለዘመናት፥ ለዘመንም እኩሌታ ነው ፤ የተቀደሰውም ሕዝብ ኀይል መበተን በተጨረሰ ጊዜ ይህ ሁሉ ይፈጸማል” ብሎ ለዘለዓለም ሕያው ሆኖ በሚኖረው ሲምል ሰማሁ።