ከዘመናትም በኋላ ይቀላቀላሉ፤ የአዜብም ንጉሥ ሴት ልጅ ቃል ኪዳን ለማድረግ ወደ መስዕ ንጉሥ ትመጣለች። የክንድዋ ኀይል ግን አይጸናም፤ ዘሩም አይጸናም፤ እርስዋና እርስዋን ያመጡ፥ የወለዳትም፥ በዚያም ዘመን ያጸናት አልፈው ይሰጣሉ።