“በፍጻሜ ዘመንም የዐዜብ ንጉሥ ከእርሱ ጋር ይዋጋል፤ የመስዕም ንጉሥ ከሠረገሎችና ከፈረሰኞች፥ ከብዙ መርከቦችም ጋር ይመጣበታል፤ ወደ ሀገሮችም ይገባል፤ ይጐርፍማል፥ ያልፍማል።