ኤርምያስም እንዲህ ሲል ተናገረ፥ “ጌታዬ ሆይ፥ እለምንሃለሁ፤ ሕዝቡን ብዙ ዘመን ለጠበቃቸው፥ እኔን ባሪያህ ኤርምያስንም ከሀገሩ ሰው ሁሉ ይልቅ ለጠበቀኝ ለኢትዮጵያዊው ለአቤሜሌክ የማደርገውን ግለጥልኝ።