የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




2 ሳሙኤል 8:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ንጉ​ሡም ዳዊት ከሶ​ቤ​ቅና ከተ​መ​ረ​ጡት ከአ​ድ​ር​አ​ዛር ከተ​ሞች እጅግ ብዙ ናስን ወሰደ። በእ​ር​ሱም ሰሎ​ሞን የብ​ረት ባሕ​ርና ምሰ​ሶ​ዎ​ችን፥ ሰኖ​ች​ንና ሌሎች ዕቃ​ዎ​ችን ሠራ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ንጉሡ ዳዊት ቤጣህና ቤሮታይ ከተባሉ ከአድርአዛር ከተሞችም እጅግ ብዙ ናስ አጋዘ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ንጉሡ ዳዊት ቤጣህና ቤሮታይ ከተባሉ ከሀዳድዔዜር ከተሞችም እጅግ ብዙ ናስ ወሰደ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እንዲሁም ንጉሥ ዳዊት ሀዳድዔዜር ከሚያስተዳድራቸው ቤጣሕና ቤሮታይ ተብለው ከሚጠሩት ከተሞች እጅግ ብዙ የሆነ ነሐስ ወሰደ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ንጉሡም ዳዊት ከአድርአዛር ከተሞች ከቤጣሕና ከቤሮታይ እጅግ ብዙ ናስ ወሰደ።

ምዕራፉን ተመልከት



2 ሳሙኤል 8:8
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዳዊ​ትም ለሱ​ባን ንጉሥ ለአ​ድ​ር​አ​ዛር አገ​ል​ጋ​ዮች የነ​በ​ሩ​ትን ጋሻ አግ​ሬ​ዎች ወሰደ፤ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም አመ​ጣ​ቸው። እነ​ዚ​ህ​ንም የግ​ብፅ ንጉሥ ሱስ​ቀም በሰ​ሎ​ሞን ልጅ በሮ​ብ​ዓም ዘመን ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም በወጣ ጊዜ ወሰ​ዳ​ቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ደግሞ ከጌ​ታው ከሱባ ንጉሥ ከአ​ድ​ር​አ​ዛር የኰ​በ​ለ​ለ​ውን የኤ​ል​ያ​ዳን ልጅ ሬዞ​ንን ጠላት አድ​ርጎ አስ​ነ​ሣ​በት።


ከዚ​ህም በኋላ ዳዊት ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን መታ፤ አዋ​ረ​ዳ​ቸ​ውም፤ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም እጅ ጌት​ንና መን​ደ​ሮ​ች​ዋን ወሰደ።


ከሚ​ጢ​ብ​ሐ​ትና ከተ​መ​ረ​ጡት ከአ​ድ​ር​አ​ዛር ከተ​ሞች ዳዊት እጅግ ብዙ ናስ ወሰደ፤ ከዚ​ህም ሰሎ​ሞን የና​ሱን ኩሬና ዓም​ዶች የና​ሱ​ንም ዕቃ ሠራ።


አሁ​ንም፥ እነሆ፥ በድ​ህ​ነቴ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት መቶ ሺህ መክ​ሊት ወር​ቅና አንድ ሚሊ​ዮን መክ​ሊት ብር፥ ሚዛ​ንም የሌ​ላ​ቸው ብዙ ናስና ብረት አዘ​ጋ​ጅ​ቻ​ለሁ፤ ደግ​ሞም የማ​ይ​ቈ​ጠር ብዙ የዝ​ግባ እን​ጨ​ትና ድን​ጋ​ዮች አዘ​ጋ​ጅ​ቻ​ለሁ፤ አን​ተም ልጄ ከዚያ በላይ ጨምር።


ቍጥር በሌ​ለው በወ​ር​ቅና ብር፥ በና​ስና ብረት ተነ​ሥ​ተህ ሥራ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከአ​ንተ ጋር ይሁን።”


ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት ሥራ አም​ስት ሺህ መክ​ሊት ወር​ቅና ዐሥር ሺህ ዳሪክ፥ ዐሥር ሺህም መክ​ሊት ብር፥ ዐሥራ ስም​ንት ሺህም መክ​ሊት ናስ፥ መቶ ሺህም መክ​ሊት ብረት ሰጡ።


ሐማት፥ ቤሮታ፥ በደ​ማ​ስቆ ድን​በ​ርና በሐ​ማት ድን​በር መካ​ከል ያለው ሲብ​ራ​ይም፥ በሐ​ው​ራን ድን​በር አጠ​ገብ ያለው ሐጸ​ር​ሃ​ቲ​ኮን።