2 ሳሙኤል 5:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም ከኬብሮን ከመጣ በኋላ እንደ ገና ቁባቶቹንና ሚስቶቹን ከኢየሩሳሌም ወሰደ፤ ለዳዊትም ደግሞ ወንዶችና ሴቶች ልጆች ተወለዱለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳዊት ከኬብሮን ከሄደ በኋላ፣ በኢየሩሳሌም ተጨማሪ ሚስቶች አገባ፤ ቁባቶችንም አስቀመጠ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችም ተወለዱለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳዊት ከኬብሮን ከመጣ በኋላ፥ ከበፊቶቹ በተጨማሪ በኢየሩሳሌም ተጨማሪ ዕቁባቶችን አስቀመጠ፤ ሚስቶችም አገባ፤ ብዙ ወንዶችና ሴቶች ልጆችም ተወለዱለት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊት ከኬብሮን ወደ ኢየሩሳሌም ከመጣ በኋላ ሌሎች ተጨማሪ ሚስቶችና ቁባቶች እንዲኖሩት አደረገ። ብዙ ወንዶችና ሴቶች ልጆችም ተወልደውለት ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም ከኬብሮን ከመጣ በኋላ ሌሎቹን ቁባቶቹንና ሚስቶቹን ከኢየሩሳሌም ወሰደ፥ ለዳዊትም ደግሞ ወንዶችና ሴቶች ልጆች ተወለዱለት። |
ዳዊትም እግዚአብሔር በእስራኤል ላይ ንጉሥ አድርጎ እንዳዘጋጀው፥ ስለ ሕዝቡ ስለ እስራኤልም መንግሥቱን ከፍ እንዳደረገ ዐወቀ።
በኬብሮን ለዳዊት የተወለዱለት ልጆች እነዚህ ናቸው። በኵሩ አምኖን ከኢይዝራኤላዊቱ ከአኪናሆም፥ ሁለተኛውም ዶለህያ ከቀርሜሎሳዊቱ ከአቢግያ፥