2 ሳሙኤል 5:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)13 ዳዊት ከኬብሮን ከመጣ በኋላ፥ ከበፊቶቹ በተጨማሪ በኢየሩሳሌም ተጨማሪ ዕቁባቶችን አስቀመጠ፤ ሚስቶችም አገባ፤ ብዙ ወንዶችና ሴቶች ልጆችም ተወለዱለት። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም13 ዳዊት ከኬብሮን ከሄደ በኋላ፣ በኢየሩሳሌም ተጨማሪ ሚስቶች አገባ፤ ቁባቶችንም አስቀመጠ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችም ተወለዱለት። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም13 ዳዊት ከኬብሮን ወደ ኢየሩሳሌም ከመጣ በኋላ ሌሎች ተጨማሪ ሚስቶችና ቁባቶች እንዲኖሩት አደረገ። ብዙ ወንዶችና ሴቶች ልጆችም ተወልደውለት ነበር፤ ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)13 ዳዊትም ከኬብሮን ከመጣ በኋላ እንደ ገና ቁባቶቹንና ሚስቶቹን ከኢየሩሳሌም ወሰደ፤ ለዳዊትም ደግሞ ወንዶችና ሴቶች ልጆች ተወለዱለት። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)13 ዳዊትም ከኬብሮን ከመጣ በኋላ ሌሎቹን ቁባቶቹንና ሚስቶቹን ከኢየሩሳሌም ወሰደ፥ ለዳዊትም ደግሞ ወንዶችና ሴቶች ልጆች ተወለዱለት። ምዕራፉን ተመልከት |