እንዲህም ሆነ፤ ወደ ማታ ጊዜ ዳዊት ከምንጣፉ ተነሣ፤ በንጉሥም ቤት በሰገነት ላይ ተመላለሰ፤ በሰገነቱም ሳለ አንዲት ሴት ስትታጠብ አየ፤ ሴቲቱም እጅግ የተዋበች መልከ መልካም ነበረች።
2 ሳሙኤል 4:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የቤሮታዊውም የሬሞን ልጆች ሬካብና በዓና ቀኑ ሲሞቅ ወደ ኢያቡስቴ ቤት መጡ፤ እርሱም በቀትር ጊዜ በአልጋው ላይ ተኝቶ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ጊዜ የብኤሮታዊው የሬሞን ልጆች ሬካብና በዓና ወደ ኢያቡስቴ ቤት ለመሄድ ዐልጋው ላይ ተኝቶ ሳለ፣ ሙቀት ሲሆን እኩለ ቀን ላይ ደረሱ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚህ ጊዜ የበኤሮታዊው የሪሞን ልጆች ሬካብና በዓና ወደ ኢያቡስቴ ቤት ለመሄድ ተነሡ፤ እርሱም የቀትር ጊዜ ዕረፍት ለማድረግ አልጋው ላይ ተኝቶ እያለ፥ እኩለ ቀን ላይ ደረሱ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሪም ልጆች ሬካብና በዓና ወደ ኢያቡስቴ ቤት በመሄድ እኩለ ቀን ላይ ደረሱ፤ እርሱም በዚያን ሰዓት የቀትር ጊዜ ዕረፍት በማድረግ ላይ ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የብኤሮታዊውም የሬሞን ልጆች ሬካብና በዓና ቀኑ ሲሞቅ ወደ ኢያቡስቴ ቤት መጡ፥ እርሱም በቀትር ጊዜ በምንጣፍ ላይ ተኝቶ ነበር። |
እንዲህም ሆነ፤ ወደ ማታ ጊዜ ዳዊት ከምንጣፉ ተነሣ፤ በንጉሥም ቤት በሰገነት ላይ ተመላለሰ፤ በሰገነቱም ሳለ አንዲት ሴት ስትታጠብ አየ፤ ሴቲቱም እጅግ የተዋበች መልከ መልካም ነበረች።
ለሳኦልም ልጅ ለኢያቡስቴ የጭፍራ አለቆች የሆኑ ሁለት ሰዎች ነበሩት፤ የአንደኛው ስም በዓና፥ የሁለተኛውም ስም ሬካብ ነበረ፤ ከብንያምም ልጆች የቤሮታዊው የሬሞን ልጆች ነበሩ፤ ቤሮትም ለብንያም ተቈጥራ ነበር።
የእኩሌቶቹ ፈረሶች አለቃ ዘምሪም አሽከሮቹን ሁሉ ሰብስቦ ዐመፀ፤ ኤላም በቴርሳ ነበረ፤ በቴርሳም በነበረው በመጋቢው በአሳ ቤት ይሰክር ነበር።
ከእርሱም ዘንድ አልፈው ከሄዱ በኋላ እጅግ ታሞ ሳለ ተዉት፤ የገዛ ባሪያዎቹም ስለ ካህኑ ስለ ኢዮአዳ ልጅ ደም ተበቅለው በአልጋው ላይ ገደሉት፤ ሞተም፤ በዳዊትም ከተማ ቀበሩት፤ ነገር ግን በነገሥታት መቃብር አልቀበሩትም።
አሜስያስም እግዚአብሔርን ከመከተል በራቀ ጊዜ በኢየሩሳሌም የዐመፅ መሐላ አደረጉበት፤ ወደ ለኪሶም ኮበለለ፤ በስተኋላውም ወደ ለኪሶ ላኩ፤ በዚያም ገደሉት።