Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 4:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ለሳ​ኦ​ልም ልጅ ለኢ​ያ​ቡ​ስቴ የጭ​ፍራ አለ​ቆች የሆኑ ሁለት ሰዎች ነበ​ሩት፤ የአ​ን​ደ​ኛው ስም በዓና፥ የሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ስም ሬካብ ነበረ፤ ከብ​ን​ያ​ምም ልጆች የቤ​ሮ​ታ​ዊው የሬ​ሞን ልጆች ነበሩ፤ ቤሮ​ትም ለብ​ን​ያም ተቈ​ጥራ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 በዚህ ጊዜ የሳኦል ልጅ ኢያቡስቴ የወራሪ ጭፍራ ቡድን መሪዎች የሆኑ ሁለት ሰዎች ነበሩት፤ አንዱ በዓና ሌላው ደግሞ ሬካብ ይባሉ ነበር። እነርሱም ከብንያም ነገድ የብኤሮት ተወላጅ የሆነው የሬሞን ልጆች ነበሩ፤ ብኤሮት ከብንያም ክፍል እንደ አንዱ ትቈጠራለች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 በዚህ ጊዜ የሳኦል ልጅ ኢያቡስቴ የወራሪ ጭፍራ ቡድን መሪዎች የሆኑ ሁለት ሰዎች ነበሩት፤ አንዱ በዓና ሌላው ደግሞ ሬካብ ይባሉ ነበር። እነርሱም የበኤሮት ተወላጅ የሆነው የሬሞን ልጆች የነበሩ ሲሆን፥ በኤሮትም ከብንያም ክፍል እንደ አንዱ ተቆጥራ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ኢያቡስቴ የወራሪ ጭፍራ ቡድን መሪዎች የሆኑ ሁለት መኰንኖች ነበሩት፤ እነርሱም ከብንያም ነገድ የበኤሮት ተወላጆች የሆኑት የሪሞን ልጆች በዓናና ሬካብ ነበሩ፤ በኤሮት የብንያም ክፍል እንደ ሆነች ይታሰብ ነበር፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ለሳኦልም ልጅ ለኢያቡስቴ የጭፍራ አለቆች የሆኑ ሁለት ሰዎች ነበሩት፥ የአንዱም ስም በዓና፥ የሁለተኛውም ስም ሬካብ ነበረ፥ ከብንያምም ልጆች የብኤሮታዊው የሬሞን ልጆች ነበሩ፥ ብኤሮትም ለብንያም ተቆጥራ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 4:2
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ገባ​ዖን፥ ራማ፥ ብኤ​ሮት፤


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ተጕ​ዘው በሦ​ስ​ተ​ኛው ቀን ወደ ከተ​ሞ​ቻ​ቸው ደረሱ፤ ከተ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም ገባ​ዖን፥ ከፊራ፥ ብኤ​ሮ​ትና ኢያ​ሪም ነበሩ።


ብዙም መብል አዘ​ጋ​ጀ​ላ​ቸው፤ በበ​ሉና በጠጡ ጊዜም አሰ​ና​በ​ታ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም ወደ ጌታ​ቸው ሄዱ። ከዚ​ያም በኋላ የሶ​ር​ያ​ው​ያን አደጋ ጣዮች ዳግ​መኛ ወደ እስ​ራ​ኤል ሀገር አል​መ​ጡም።


ከሶ​ር​ያ​ው​ያ​ንም ጋር ወደ ሰልፍ በወጣ ጊዜ ከእ​ስ​ራ​ኤል ምድር ታናሽ ብላ​ቴና ሴት ማረከ፤ ለሚ​ስ​ቱም አገ​ል​ጋይ አደ​ረ​ጋት።


በዚያ ጊዜም የዳ​ዊት ብላ​ቴ​ኖ​ችና ኢዮ​አብ ከዘ​መቻ ታላቅ ምርኮ ይዘው መጡ። አበ​ኔር ግን ዳዊት አሰ​ና​ብ​ቶት በደ​ኅና ሄዶ ነበር እንጂ በኬ​ብ​ሮን አል​ነ​በ​ረም።


የቤ​ሮ​ታ​ዊ​ውም የሬ​ሞን ልጆች ሬካ​ብና በዓና ቀኑ ሲሞቅ ወደ ኢያ​ቡ​ስቴ ቤት መጡ፤ እር​ሱም በቀ​ትር ጊዜ በአ​ል​ጋው ላይ ተኝቶ ነበር።


ዳዊ​ትም ለቤ​ሮ​ታ​ዊው ለሬ​ሞን ልጆች ለሬ​ካ​ብና ለወ​ን​ድሙ ለበ​ዓና እን​ዲህ ብሎ መለ​ሰ​ላ​ቸው፥ “ነፍ​ሴን ከመ​ከራ ሁሉ ያዳነ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን!


አሞ​ና​ዊው ኤልዩ፥ የሶ​ር​ህያ ልጅ የኢ​ዮ​አብ ጋሻ ጃግሬ ቤሮ​ታ​ዊው ጌሎሬ፥


ማሴማ፥ ቤሮን፥ አሞቂ፥


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች