ለሳኦልም ልጅ ለዮናታን አንድ ሽባ የሆነ ልጅ ነበረው። የሳኦልና የዮናታን ወሬ ከኢይዝራኤል በመጣ ጊዜ የአምስት ዓመት ልጅ ነበረ፤ ሞግዚቱም አዝላው ሸሸች፤ ልትሸሽም ስትሮጥ ወድቆ ሽባ ሆነ። ስሙም ሜምፌቡስቴ ነበረ።
2 ሳሙኤል 4:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቤሮታውያንም ወደ ጌቴም ሸሽተው ነበር፤ እስከ ዛሬም ድረስ በዚያ ተጠግተው ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የብኤሮት ሕዝብ ወደ ጊቴም በመሸሽ እስከ ዛሬም በመጻተኛነት እዚያው ይኖራልና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የበኤሮት ሕዝብ ወደ ጊታይም በመሸሽ እስከ ዛሬም በመጻተኝነት እዚያው ይኖራሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የበኤሮት የመጀመሪያዎቹ ነዋሪዎችም ወደ ጊታይም ተሰደው ከዚያን ዘመን ጀምሮ የሚኖሩት በዚያው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ብኤሮታውያንም ወደ ጌቴም ሸሽተው ነበር፥ እስከ ዛሬም ድረስ በዚያ ተጠግተው ነበር። |
ለሳኦልም ልጅ ለዮናታን አንድ ሽባ የሆነ ልጅ ነበረው። የሳኦልና የዮናታን ወሬ ከኢይዝራኤል በመጣ ጊዜ የአምስት ዓመት ልጅ ነበረ፤ ሞግዚቱም አዝላው ሸሸች፤ ልትሸሽም ስትሮጥ ወድቆ ሽባ ሆነ። ስሙም ሜምፌቡስቴ ነበረ።
በሸለቆውም ማዶና በዮርዳኖስ ማዶ የነበሩ እስራኤላውያን የእስራኤል ሰዎች እንደ ሸሹ፥ ሳኦልና ልጆቹም እንደ ሞቱ ባዩ ጊዜ ከተሞቹን ለቅቀው ሸሹ፤ ፍልስጥኤማውያንም መጥተው ተቀመጡባቸው።