2 ሳሙኤል 4:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም ጐልማሶቹን አዘዘ፤ ገደሉአቸውም፤ እጆቻቸውንና እግሮቻቸውን ቈርጠው በኬብሮን በውኃ መቆሚያ አጠገብ አንጠለጠሉአቸው። የኢያቡስቴን ራስ ግን ወስደው በአበኔር መቃብር በኬብሮን ቀበሩት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህም ዳዊት የራሱን ሰዎች አዘዘ፤ እነርሱንም ገደሏቸው፤ እጅና እግራቸውንም ቈርጠው በኬብሮን ካለው ኵሬ አጠገብ ሰቀሏቸው። ነገር ግን የኢያቡስቴን ራስ ወስደው ኬብሮን በሚገኘው በአበኔር መቃብር አጠገብ ቀበሩት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህም ዳዊት የራሱን ሰዎች አዘዘ፤ እነርሱንም ገደሏቸው፤ እጅና እግራቸውንም ቆርጠው በኬብሮን ካለው ኲሬ አጠገብ ሰቀሏቸው። ነገር ግን የኢያቡስቴን ራስ ወስደው ኬብሮን በሚገኘው በአበኔር መቃብር አጠገብ ቀበሩት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወዲያውም ዳዊት እንዲገድሉአቸው ለወታደሮቹ ትእዛዝ አስተላለፈ፤ ወታደሮቹም ሬካብንና በዓናን ገደሉአቸው፤ እጃቸውንና እግራቸውንም ቈርጠው በኬብሮን በሚገኘው ኲሬ አጠገብ እንጨት ላይ ሰቀሉአቸው፤ የኢያቡስቴንም ራስ ወስደው በዚያው በኬብሮን በሚገኘው በአበኔር መቃብር ውስጥ ቀበሩት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም ጕልማሶቹን አዘዘ፥ ገደሉአቸውም፥ እጃቸውንና እግራቸውን ቆርጠው በኬብሮን በውኃ መቆሚያ አጠገብ አንጠለጠሉአቸው። የኢያቡስቴንም ራስ ወስደው በአበኔር መቃብር በኬብሮን ቀበሩት። |
በፋንታው ነግሠሃልና እግዚአብሔር የሳኦልን ቤት ደም ሁሉ መለሰብህ፤ እግዚአብሔርም መንግሥትህን ለልጅህ ለአቤሴሎም እጅ አሳልፎ ሰጥቶታል፤ እነሆም፥ አንተ የደም ሰው ነህና በመከራ ተይዘሃል።”
በገባዖንም ሰዎች እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፤ በእግዚአብሔርም ፊት በተራራው ላይ ሰቀሏቸው። ሰባቱም በአንድነት ወደቁ፤ እህል በሚታጨድበትም ወራት በገብሱ መከር መጀመሪያ ተገደሉ።
አበኔርንም በኬብሮን ቀበሩት፤ ንጉሡም ድምፁን ከፍ አድርጎ በመቃብሩ አጠገብ አለቀሰ፤ ሕዝቡም ሁሉ ለአበኔር አለቀሱለት።