የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




2 ሳሙኤል 24:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ወደ ገለ​ዓ​ድም አዳ​ሳይ ወደ​ም​ት​ባል ወደ ተባ​ሶን ሀገ​ርም መጡ፤ ወደ ዳኒ​ዳ​ንና ወደ ኡዳ​ንም ደረሱ፤ ወደ ሲዶ​ናም ዞሩ፤

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እንዲሁም ወደ ገለዓድና ወደ ተባሶን አዳሰይ፣ ቀጥሎም ወደ ዳንየዓን ከዚያም ዞረው ወደ ሲዶና ሄዱ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እንዲሁም ወደ ገለዓድና በሒታውያን ግዛት ወዳለው ወደ ቃዴስ ዘለቁ፤ ከዚያም ወደ ዳን፥ ከዳንም ወደ ሲዶና ዞሩ፤

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ቀጥለውም ወደ ገለዓድና በሒታውያን ግዛት ውስጥ ወዳለው ወደ ቃዴስ ዘለቁ፤ ከዚያም በኋላ ወደ ዳን፥ ከዳንም ወደ ምዕራብ ታጥፈው ወደ ሲዶና ሄዱ፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ወደ ገለዓድም ወደ ተባሶን አዳሰይ አገር መጡ፥ ወደ ዳንየዓንም ደረሱ፥ ወደ ሲዶናም ዞሩ፥

ምዕራፉን ተመልከት



2 ሳሙኤል 24:6
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከነ​ዓ​ንም የበ​ኵር ልጁን ሲዶ​ንን፥ ኬጤ​ዎ​ንን፥


እር​ሱም ያለ​ውን ሁሉ ይዞ ኰበ​ለለ፤ ተነ​ሥ​ቶም ወን​ዙን ተሻ​ገረ፤ በገ​ለ​ዓድ ተራ​ራም አደረ።


ለሮ​ቤል ልጆ​ችና ለጋድ ልጆች እጅግ ብዙ እን​ስ​ሶች ነበ​ሩ​አ​ቸው፤ እነ​ሆም፥ የኢ​ያ​ዜር ምድ​ርና የገ​ለ​ዓድ ምድር የከ​ብት ሀገር እንደ ነበረ አዩ።


የም​ና​ሴም ልጅ የማ​ኪር ልጅ ወደ ገለ​ዓድ ሄዶ ገለ​ዓ​ድን ያዘ፤ በእ​ር​ስ​ዋም የነ​በ​ሩ​ትን አሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንን አጠፋ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ስ​ራ​ኤል እጅ አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው፤ መቱ​አ​ቸ​ውም፤ ወደ ታላ​ቂ​ቱም ሲዶና፥ ወደ ማሴ​ሮ​ንም፥ በም​ሥ​ራ​ቅም በኩል ወዳ​ለው ወደ ሞሳሕ ሸለቆ አሳ​ደ​ዱ​አ​ቸው፤ ማን​ንም ሳያ​ስ​ቀሩ መቱ​አ​ቸው።


ከዚ​ያም ወደ ኤብ​ሮን፥ ወደ ረዓብ፥ ወደ አሜ​ማ​ህን፥ ወደ ቀን​ታን እስከ ታላቁ ሲዶና ይደ​ር​ሳል።


የዳን ልጆች ነገድ ርስት በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው እነ​ዚህ ከተ​ሞ​ችና መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸው ናቸው። የዳን ልጆ​ችም በተ​ራ​ራው ላይ የሚ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቋ​ቸው አሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንን አላ​ስ​ጨ​ነ​ቁ​አ​ቸ​ውም። አሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም ወደ ሸለ​ቆ​ዎች ይወ​ርዱ ዘንድ አል​ፈ​ቀ​ዱ​ላ​ቸ​ውም። ከእ​ነ​ር​ሱም ከር​ስ​ታ​ቸው ዳርቻ አንድ ክፍ​ልን ወሰዱ።


አሴ​ርም የዓኮ ነዋ​ሪ​ዎ​ችን አላ​ጠ​ፋ​ቸ​ውም፤ ነገር ግን ገባ​ሮች ሆኑ​ላ​ቸው፤ የዶር ነዋ​ሪ​ዎ​ች​ንና የሲ​ዶን ነዋ​ሪ​ዎ​ችን፥ የደ​ላ​ፍ​ንም ነዋ​ሪ​ዎች፥ የአ​ክ​ሶ​ዚ​ብ​ንና የሄ​ል​ባን፥ የአ​ፌ​ቅ​ንና የረ​ዓ​ብ​ንም ሰዎች አላ​ጠ​ፉ​አ​ቸ​ውም።