የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




2 ሳሙኤል 19:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ኢዮ​አ​ብም ወደ ንጉሡ ወደ ቤት ገብቶ እን​ዲህ አለ፥ “ዛሬ ነፍ​ስ​ህ​ንና የወ​ን​ዶ​ች​ንና የሴ​ቶች ልጆ​ች​ህን ነፍስ፥ የሚ​ስ​ቶ​ች​ህ​ንና የቁ​ባ​ቶ​ች​ህን ነፍስ ያዳ​ኑ​ትን የአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ች​ህን ሁሉ ፊት በዚች ቀን አሳ​ፍ​ረ​ሃል።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዚያም ኢዮአብ ወደ ንጉሡ ቤት ገብቶ እንዲህ አለው፤ “የአንተን፣ የወንዶችንና የሴቶች ልጆችህን፣ የሚስቶችህንና የቁባቶችህን ሕይወት ያተረፉትን ሰዎች ሁሉ ዛሬ አሳፍረሃቸዋል።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ንጉሡ ፊቱን ሸፍኖ፥ “ልጄ አቤሴሎም ሆይ፥ ልጄ አቤሴሎም፥ ልጄ ሆይ፥ ልጄን! ልጄን!” እያለ በታላቅ ድምፅ ጮኸ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በዚህ ጊዜ ኢዮአብ ወደ ንጉሡ ቤት ሄዶ እንዲህ አለው፤ “የአንተን የወንዶችና የሴቶች ልጆችህን፥ የሚስቶችህንና የቊባቶችህን ሕይወት ያዳኑትን ሰዎች ዛሬ አሳፍረሃቸዋል፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ኢዮአብም ወደ ንጉሡ ወደ ቤት ገብቶ እንዲህ አለ፦ ዛሬ ነፍስህንና የወንዶችና የሴቶች ልጆችህን ነፍስ የሚስቶችህንና የቁባቶችህን ነፍስ ያዳኑትን የባሪያዎችህን ሁሉ ፊት ዛሬ አሳፍረሃል፥

ምዕራፉን ተመልከት



2 ሳሙኤል 19:5
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዳዊ​ትም ወደ ደብረ ዘይት ዐቀ​በት ወጣ፤ ሲወ​ጣም ያለ​ቅስ ነበር፤ ራሱ​ንም ተከ​ና​ንቦ ነበር፤ ያለ​ጫ​ማም ይሄድ ነበር፤ ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በ​ሩት ሕዝብ ሁሉ ተከ​ና​ን​በው ነበር፤ እያ​ለ​ቀ​ሱም ይወጡ ነበር።


አቤ​ሴ​ሎ​ም​ንም ወስዶ በበ​ረሓ ባለ በታ​ላቅ ገደል ውስጥ ጣለው፤ እጅ​ግም ታላቅ የሆነ የድ​ን​ጋይ ክምር ከመ​ረ​በት፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ሸሽ​ተው ወደ ድን​ኳ​ና​ቸው ገቡ።


ለአ​ሚ​ሳ​ይም፦ አንተ የአ​ጥ​ንቴ ፍላ​ጭና የሥ​ጋዬ ቍራጭ አይ​ደ​ለ​ህ​ምን? በዘ​መ​ን​ህም ሁሉ በኢ​ዮ​አብ ፋንታ በፊቴ የሠ​ራ​ዊት አለቃ ሳት​ሆን ብት​ቀር ዛሬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን ያድ​ር​ግ​ብኝ፤ ይህ​ንም ይጨ​ም​ር​ብኝ በሉት።”


ንጉ​ሡም ፊቱን ሸፈነ፤ ንጉ​ሡም በታ​ላቅ ድምፅ፥ “ልጄ አቤ​ሴ​ሎም፥ አቤ​ሴ​ሎም፥ ልጄ” እያለ ይጮህ ነበር።


አንተ የሚ​ጠ​ሉ​ህን ትወ​ድ​ዳ​ለህ፤ የሚ​ወ​ድ​ዱ​ህ​ንም ትጠ​ላ​ለህ፤ አለ​ቆ​ች​ህና አገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ እን​ደ​ማ​ይ​ጠ​ቅ​ሙህ እን​ደ​ም​ታ​ስብ ዛሬ ገል​ጠ​ሃ​ልና፤ አቤ​ሴ​ሎ​ምም ድኖ ቢሆን ዛሬ እኛ ሁላ​ችን እን​ሞት እንደ ነበር አው​ቃ​ለሁ። ይህ በፊ​ትህ ላንተ ቀና ነበ​ረና።


እኔም ዛሬ ዘመዱ እንደ ሆንሁ፥ እር​ሱም በን​ጉሡ ዘንድ የተ​ሾመ እንደ ሆነ አታ​ው​ቁ​ምን? እነ​ዚ​ህም ሰዎች የሦ​ር​ህያ ልጆች በር​ት​ተ​ው​ብ​ኛል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክፋት በሠራ ላይ እንደ ክፋቱ ይመ​ል​ስ​በት” አላ​ቸው።


ስለ​ዚህ በሚ​ያ​ሠ​ቃ​ዩ​አ​ቸው ሰዎች እጅ አሳ​ል​ፈህ ሰጠ​ሃ​ቸው፤ አስ​ጨ​ነ​ቋ​ቸ​ውም፤ በመ​ከ​ራ​ቸ​ውም ጊዜ ወደ አንተ ጮኹ፤ ከሰ​ማ​ይም ሰማ​ሃ​ቸው፤ እንደ ምሕ​ረ​ት​ህም ብዛት ታዳ​ጊ​ዎ​ችን ሰጠ​ሃ​ቸው፤ ከሚ​ያ​ሠ​ቃ​ዩ​አ​ቸ​ውም እጅ አዳ​ን​ሃ​ቸው።


ማዳን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፥ በረ​ከ​ት​ህም በሕ​ዝ​ብህ ላይ ነው።