የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




2 ሳሙኤል 19:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ንጉ​ሡም ፊቱን ሸፈነ፤ ንጉ​ሡም በታ​ላቅ ድምፅ፥ “ልጄ አቤ​ሴ​ሎም፥ አቤ​ሴ​ሎም፥ ልጄ” እያለ ይጮህ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ንጉሡ ፊቱን ሸፍኖ፣ “ልጄ አቤሴሎም ሆይ፤ ልጄን! ወየው ልጄን!” እያለ ጮኸ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በዚያችም ዕለት ከጦርነት ሸሽቶ በኀፍረት እየተሸማቀቀ ወደ ከተማ እንደሚገባ ሰው ሕዝቡም ድምፅ ሳያሰማ ወደ ከተማ ገባ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ንጉሡም ፊቱን ሸፍኖ “ልጄ ሆይ! ልጄ አቤሴሎም! አቤሴሎም ልጄ!” እያለ ድምፁን ከፍ አድርጎ ያለቅስ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ንጉሡም ፊቱን ሸፈነ፥ ንጉሡም በታላቅ ድምፅ፦ ልጄ አቤሴሎም ሆይ፥ ልጄ አቤሴሎም፥ ልጄ ሆይ እያለ ይጮኽ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት



2 ሳሙኤል 19:4
5 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የሶ​ር​ህያ ልጅ ኢዮ​አ​ብም የን​ጉሡ ልብ ወደ አቤ​ሴ​ሎም እን​ዳ​ዘ​ነ​በለ ዐወቀ።


ዳዊ​ትም ወደ ደብረ ዘይት ዐቀ​በት ወጣ፤ ሲወ​ጣም ያለ​ቅስ ነበር፤ ራሱ​ንም ተከ​ና​ንቦ ነበር፤ ያለ​ጫ​ማም ይሄድ ነበር፤ ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በ​ሩት ሕዝብ ሁሉ ተከ​ና​ን​በው ነበር፤ እያ​ለ​ቀ​ሱም ይወጡ ነበር።


ንጉ​ሡም እጅግ ደነ​ገጠ፤ በበ​ሩም ላይ ወዳ​ለ​ችው ሰገ​ነት ወጥቶ አለ​ቀሰ፤ ሲሄ​ድም፥ “ልጄ አቤ​ሴ​ሎም ሆይ፥ ልጄ፥ ልጄ አቤ​ሴ​ሎም ሆይ፥ በአ​ንተ ፋንታ እኔ እን​ድ​ሞት ቤዛ​ህም እን​ድ​ሆን ማን ባደ​ረ​ገኝ፥ ልጄ አቤ​ሴ​ሎም፥ ልጄ ሆይ፥” ይል ነበር።


ከሰ​ልፍ በሸሸ ጊዜ ያፈረ ሕዝብ ተሰ​ርቆ እን​ደ​ሚ​ገባ በዚያ ቀን ሕዝቡ ተሰ​ር​ቀው ወደ ከተማ ገቡ።


ኢዮ​አ​ብም ወደ ንጉሡ ወደ ቤት ገብቶ እን​ዲህ አለ፥ “ዛሬ ነፍ​ስ​ህ​ንና የወ​ን​ዶ​ች​ንና የሴ​ቶች ልጆ​ች​ህን ነፍስ፥ የሚ​ስ​ቶ​ች​ህ​ንና የቁ​ባ​ቶ​ች​ህን ነፍስ ያዳ​ኑ​ትን የአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ች​ህን ሁሉ ፊት በዚች ቀን አሳ​ፍ​ረ​ሃል።