የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




2 ሳሙኤል 18:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ከዚ​ያም ጦሩ በሀ​ገሩ ሁሉ ፊት ተበ​ተነ፤ በዚ​ያም ቀን በሰ​ይፍ ከተ​ገ​ደ​ሉት ሕዝብ ይልቅ በበ​ረሓ የሞቱ ይበ​ዛሉ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ውጊያው በገጠሩ ሁሉ ተስፋፋ፤ በዚያ ቀን ሰይፍ ከጨረሰው ይልቅ ጫካ ውጦ ያስቀረው ሰው በለጠ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ውጊያው በአገሩ ሁሉ ተስፋፋ፤ በዚያን ቀን ሰይፍ ከጨረሰው ይልቅ ጫካ ውጦ ያስቀረው ሰው በለጠ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ጦርነቱም በየገጠሩ ስለ ተስፋፋ በጦርነት ከሞቱት ሰዎች ይልቅ በደን ውስጥ ያለቁት ቊጥራቸው በዛ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ከዚያም ሰልፉ በአገሩ ሁሉ ፊት ላይ ተበተነ፥ በዚያም ቀን ሰይፍ ከዋጠው ሕዝብ ይልቅ ዱር ብዙ ዋጠ።

ምዕራፉን ተመልከት



2 ሳሙኤል 18:8
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በዚ​ያም የእ​ስ​ራ​ኤል ሕዝብ በዳ​ዊት አገ​ል​ጋ​ዮች ፊት ወደቁ፤ በዚ​ያም ቀን ታላቅ ውጊያ በዚያ ሆነ፤ ሃያ ሺህ ሰዎ​ችም ሞቱ።


አቤ​ሴ​ሎ​ምም ከዳ​ዊት አገ​ል​ጋ​ዮች ጋር ተገ​ናኘ፤ አቤ​ሴ​ሎ​ምም በበ​ቅሎ ተቀ​ምጦ ነበር፤ በቅ​ሎ​ውም ብዙ ቅር​ን​ጫፍ ባለው በታ​ላቅ ዛፍ በታች ገባ፤ ራሱም በዛፉ ተያዘ፤ በሰ​ማ​ይና በም​ድ​ርም መካ​ከል ተን​ጠ​ለ​ጠለ፤ ተቀ​ም​ጦ​በ​ትም የነ​በ​ረው በቅሎ በበ​ታቹ አለፈ።


ተነሥ፥ አቤቱ፥ አም​ላኬ ሆይ፥ አድ​ነኝ፤ አንተ በከ​ንቱ የሚ​ጠ​ሉ​ኝን ሁሉ መት​ተ​ሃ​ልና፥ የኃ​ጥ​ኣ​ን​ንም ጥርስ ሰብ​ረ​ሃ​ልና።


አቤቱ፥ በጆ​ሮ​አ​ችን ሰማን፥ አባ​ቶ​ቻ​ች​ንም በዘ​መ​ና​ቸው በቀ​ድሞ ዘመን የሠ​ራ​ኸ​ውን ሥራ ነገ​ሩን።


ነፋ​ስ​ህን ላክህ፤ ባሕ​ርም ከደ​ና​ቸው፤ በብዙ ውኆች ውስጥ እንደ አረር ሰጠሙ።


ልጄ ሆይ፥ እግዚአብሔርንና ንጉሥን ፍራ፥ ከእነርሱ ለአንዱ ስንኳ እንቢ አትበል።


እነርሱ ኀጢአተኞችን ድንገት ይበቀሏቸዋልና፤ የሁለቱንስ ፍርድ ማን ያውቃል?


ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ፊት እየ​ሸሹ በቤ​ት​ሖ​ሮን ቍል​ቍ​ለት ሲወ​ርዱ፥ ወደ ዓዜ​ቃና ወደ መቄዳ እስ​ኪ​ደ​ርሱ ድረስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሰ​ማይ ታላ​ላቅ የበ​ረዶ ድን​ጋይ አወ​ረ​ደ​ባ​ቸ​ውና ሞቱ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በሰ​ይፍ ከገ​ደ​ሉ​አ​ቸው ይልቅ በበ​ረዶ ድን​ጋይ የሞ​ቱት በለጡ።