ኢዮአብም ለነገረው ሰው፥ “እነሆ፥ ካየኸው ለምን በምድር ላይ አልገደልኸውም? ዐሥር ብርና አንድ ድግ እሰጥህ ነበር” አለው።
2 ሳሙኤል 18:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰውየውም ኢዮአብን፥ “ንጉሡ አንተንና አቢሳን፥ ኤቲንም፦ ብላቴናውን አቤሴሎምን ጠብቁ ብሎ ሲያዝ እኛ በጆሮአችን ሰምተናልና ሺህ ሰቅል ብር በእጄ ላይ ብትመዝን እጄን በንጉሡ ልጅ ላይ አልዘረጋም ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰውየው ግን ለኢዮአብ እንዲህ አለው፤ “እኛ እየሰማን ንጉሡ፣ ‘ወጣቱ አቤሴሎም ጕዳት እንዳያገኘው ስለ እኔ ብላችሁ ጠብቁት’ ብሎ አንተን፣ አቢሳንና ኢታይን ያዘዛችሁ ስለ ሆነ፣ አንድ ሺሕ ሰቅል ጥሬ ብር በእጄ ላይ ቢመዘንልኝ እንኳ፣ በንጉሡ ልጅ ላይ እጄን አላነሣም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰውየው ግን ለኢዮአብ እንዲህ አለ፤ “እኛ እየሰማን ንጉሡ፥ ‘ወጣቱ አቤሴሎም ጉዳት እንዳያገኘው ስለ እኔ ብላችሁ ጠብቁት’ ተብሎ አንተን፥ አቢሳንና ኢታይን ያዘዛችሁ ስለሆነ፥ አንድ ሺህ ብር በእጄ ላይ ቢመዘንልኝ እንኳ፥ በንጉሡ ልጅ ላይ እጄን አላነሣም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰውየው ግን እንዲህ ሲል መለሰ፤ “አንድ ሺህ ጥሬ ብር እንኳ ብትሰጠኝ በንጉሡ ልጅ ላይ እጄን አላነሣም፤ ንጉሡ ለአንተ፥ ለአቢሳና ለኢታይ ‘ለእኔ ስትሉ በወጣቱ አቤሴሎም ላይ ለሞት የሚያደርስ ጒዳት እንዳታደርሱበት’ ሲል የሰጣችሁን ትእዛዝ ሁላችንም ሰምተናል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰውዮውም ኢዮአብን፦ እኛ ስንሰማ ንጉሡ አንተንና አቢሳን ኢታይንም፦ ብላቴናውን አቤሴሎምን ማንም እንዳይነካው ተጠንቀቁ ብሎ አዝዞአልና ሺህ ብር በእጄ ላይ ብትመዝን እጄን በንጉሡ ልጅ ላይ ባልዘረጋሁም ነበር አለው። |
ኢዮአብም ለነገረው ሰው፥ “እነሆ፥ ካየኸው ለምን በምድር ላይ አልገደልኸውም? ዐሥር ብርና አንድ ድግ እሰጥህ ነበር” አለው።
ንጉሡም ኢዮአብንና አቢሳን ኤቲንም፥ “ለብላቴናው ለአቤሴሎም ስለ እኔ ራሩለት” ብሎ አዘዛቸው። ንጉሡም ስለ አቤሴሎም አለቆቹን ሁሉ ሲያዝዝ ሕዝቡ ሁሉ ሰሙ።