Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 18:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ንጉ​ሡም ኢዮ​አ​ብ​ንና አቢ​ሳን ኤቲ​ንም፥ “ለብ​ላ​ቴ​ናው ለአ​ቤ​ሴ​ሎም ስለ እኔ ራሩ​ለት” ብሎ አዘ​ዛ​ቸው። ንጉ​ሡም ስለ አቤ​ሴ​ሎም አለ​ቆ​ቹን ሁሉ ሲያ​ዝዝ ሕዝቡ ሁሉ ሰሙ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ንጉሡም ኢዮአብን፣ አቢሳንና ኢታይን፣ “ለእኔ ስትሉ በወጣቱ ልጄ በአቤሴሎም ላይ ጕዳት እንዳታደርሱበት” ብሎ አዘዛቸው። ንጉሡ ልጁን አቤሴሎምን አስመልክቶ ለእያንዳንዱ አዛዥ ትእዛዝ ሲሰጥ ሰራዊቱ ሁሉ ሰማ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ንጉሡም ኢዮአብን፥ አቢሳንና ኢታይን፥ “ለእኔ ስትሉ በወጣቱ ልጄ በኤቤሴሎም ላይ ጉዳት እንዳታደርሱበት” ብሎ አዘዛቸው። ንጉሡ ልጁን አቤሴሎምን አስመልክቶ ለአዛዥዎቹ ትእዛዝ ሲሰጥ ሕዝቡ ሁሉ ሰማ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ለኢዮአብ፥ ለአቢሳና ለኢታይም “ለእኔ ስትሉ በወጣቱ በአቤሴሎም ላይ ለሞት የሚያደርስ ጒዳት እንዳታደርሱበት” የሚል ትእዛዝ ሰጣቸው፤ ዳዊት ይህን ትእዛዝ ለጦር አዛዦቹ በሰጠ ጊዜም ወታደሮቹ ሁሉ ይሰሙ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ንጉሡም ኢዮአብንና አቢሳን ኢታይንም፦ ለብላቴናው ለአቤሴሎም ስለ እኔ ራሩለት ብሎ አዘዛቸው። ንጉሡም ስለ አቤሴሎም አለቆቹን ሁሉ ሲያዝዝ ሕዝቡ ሁሉ ሰማ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 18:5
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዳዊ​ትም አቢ​ሳ​ንና አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹን ሁሉ፥ “እነሆ፥ ከወ​ገቤ የወ​ጣው ልጄ ነፍ​ሴን ይሻል፤ ይል​ቁ​ንስ ይህ የኢ​ያ​ሚን ልጅ እን​ዴት ነዋ? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አዝ​ዞ​ታ​ልና ተዉት፥ ይር​ገ​መኝ።


አቤ​ሴ​ሎ​ምና የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች ሁሉ “የአ​ር​ካ​ዊው የኩሲ ምክር ከአ​ኪ​ጢ​ፌል ምክር ይሻ​ላል” አሉ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በአ​ቤ​ሴ​ሎም ላይ ክፉ ያመጣ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​ካ​ሚ​ቱን የአ​ኪ​ጦ​ፌ​ልን ምክር እን​ዲ​በ​ትን አዘዘ።


ሰው​የ​ውም ኢዮ​አ​ብን፥ “ንጉሡ አን​ተ​ንና አቢ​ሳን፥ ኤቲ​ንም፦ ብላ​ቴ​ና​ውን አቤ​ሴ​ሎ​ምን ጠብቁ ብሎ ሲያዝ እኛ በጆ​ሮ​አ​ችን ሰም​ተ​ና​ልና ሺህ ሰቅል ብር በእጄ ላይ ብት​መ​ዝን እጄን በን​ጉሡ ልጅ ላይ አል​ዘ​ረ​ጋም ነበር።


ለኢ​ዮ​አብ፥ “ንጉሡ ስለ አቤ​ሴ​ሎም ያዝ​ናል፤ ያለ​ቅ​ሳ​ልም” ብለው ነገ​ሩት።


ተራ​ሮ​ችን ከው​ስ​ጣ​ቸው የሚ​ያ​ጠ​ጣ​ቸው፤ ከሥ​ራህ ፍሬ ምድር ትጠ​ግ​ባ​ለች።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “አባት ሆይ፥ የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ትን ኣያ​ው​ቁ​ምና ይቅር በላ​ቸው” አለ፤ በል​ብ​ሱም ላይ ዕጣ ተጣ​ጣ​ሉና ተካ​ፈሉ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች