የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




2 ሳሙኤል 18:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ዳዊ​ትም ከእ​ርሱ ጋር የነ​በ​ሩ​ትን ሕዝብ ቈጠረ፤ የሻ​ለ​ቆ​ች​ንና የመቶ አለ​ቆ​ች​ንም በላ​ያ​ቸው ሾመ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ዳዊት ዐብሮት የነበረውን ሕዝብ ቈጠረ፤ የሻለቆችንና የመቶ አለቆችን ሾመላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ዳዊት አብሮት የነበረውን ሕዝብ ቆጠረ፤ የሻለቆችንና የመቶ አለቆችን ሾመላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ንጉሥ ዳዊት ተከታዮቹን ሁሉ በአንድነት ከሰበሰበ በኋላ በሺህና በመቶ መድቦ ለእያንዳንዱ ቡድን የጦር መኰንን ሾመ፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ዳዊትም ከእርሱ ጋር የነበሩትን ሕዝብ ቈጠረ፥ ሻለቆችንና የመቶ አለቆችንም ሾመላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት



2 ሳሙኤል 18:1
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሙሴም ኢያ​ሱን፥ “ጐል​ማ​ሶ​ችን ለአ​ንተ ምረጥ፤ ሲነ​ጋም ወጥ​ተህ ከዐ​ማ​ሌቅ ጋር ተዋጋ፤ እኔም በተ​ራ​ራው ራስ ላይ እቆ​ማ​ለሁ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በትር በእጄ ናት” አለው።


አን​ተም ከሕ​ዝቡ ሁሉ ኀያ​ላን ሰዎ​ችን፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈ​ሩ​ትን እው​ነ​ተ​ኞች ሰዎ​ችን፥ ትዕ​ቢ​ት​ንም የሚ​ጠሉ ሰዎ​ችን ፈልግ። ከእ​ነ​ር​ሱም የሺህ አለ​ቆ​ችን፥ የመቶ አለ​ቆ​ችን፥ የአ​ምሳ አለ​ቆ​ችን፥ የዐ​ሥ​ርም አለ​ቆ​ችን ሹም​ላ​ቸው።


ሙሴም ከእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ችሎታ ያላ​ቸ​ውን ሰዎች መረጠ፤ በሕ​ዝ​ቡም ላይ የሺህ አለ​ቆች፥ የመቶ አለ​ቆች፥ የአ​ም​ሳም አለ​ቆች፥ የዐ​ሥ​ርም አለ​ቆች አድ​ርጎ ሾማ​ቸው።


ሙሴም ከዘ​መቻ በተ​መ​ለ​ሱት በጭ​ፍራ አለ​ቆች፥ በሻ​ለ​ቆ​ችና በመቶ አለ​ቆች ላይ ተቈጣ።


ጸሐ​ፍ​ቱም ለሕ​ዝቡ ነግ​ረው በጨ​ረሱ ጊዜ ከታ​ላ​ላቁ ሕዝብ መካ​ከል የሠ​ራ​ዊት አለ​ቆ​ችን ይሹሙ።


ኢያ​ሱም ማልዶ ተነሣ፤ ሕዝ​ቡ​ንም አያ​ቸው፤ እር​ሱም፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ከሕ​ዝቡ በፊት ወደ ጋይ ወጡ።


ሳኦ​ልም በአ​ጠ​ገቡ የቆ​ሙ​ትን ብላ​ቴ​ኖች፥ “ብን​ያ​ማ​ው​ያን ሆይ! እን​ግ​ዲህ ስሙ በእ​ው​ነት የእ​ሴይ ልጅ እር​ሻና የወ​ይን ቦታ ለሁ​ላ​ችሁ ይሰ​ጣ​ች​ኋ​ልን? ሁላ​ች​ሁ​ንስ መቶ አለ​ቆ​ችና ሻለ​ቆች ያደ​ር​ጋ​ች​ኋ​ልን?


ለራ​ሱም የሻ​ለ​ቆ​ችና የመቶ አለ​ቆች የአ​ምሳ አለ​ቆ​ችም ያደ​ር​ጋ​ቸ​ዋል፤ እር​ሻ​ው​ንም የሚ​ያ​ርሱ፥ እህ​ሉ​ንም የሚ​ያ​ጭዱ፥ ፍሬ​ው​ንም የሚ​ለ​ቅሙ፥ የጦር መሣ​ሪ​ያ​ው​ንና የሰ​ረ​ገ​ሎ​ቹ​ንም ዕቃ የሚ​ሠሩ ያደ​ር​ጋ​ቸ​ዋል።