አቤሴሎምና የእስራኤልም ሰዎች ሁሉ “የአርካዊው የኩሲ ምክር ከአኪጢፌል ምክር ይሻላል” አሉ። እግዚአብሔርም በአቤሴሎም ላይ ክፉ ያመጣ ዘንድ እግዚአብሔር መልካሚቱን የአኪጦፌልን ምክር እንዲበትን አዘዘ።
2 ሳሙኤል 17:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ከተማም ቢገባ እስራኤል ሁሉ ወደዚያች ከተማ ገመድ ይወስዳሉ፤ እኛም አንድ ድንጋይ እንኳን እስከማይገኝባት ድረስ ወደ ወንዙ ውስጥ እንስባታለን።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከአንዲቱ ከተማ ቢገባ፣ እስራኤል ሁሉ ገመድ አምጥቶ አንድ ድንጋይ እንኳ እስከማይቀር ድረስ፣ ከተማዪቱን ወደ ሸለቆ ስበን እንከታታለን።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከአንዲቱ ከተማ ቢገባ፥ እስራኤል ሁሉ ገመድ አምጥቶ አንድ ድንጋይ እንኳ እስከማይቀር ድረስ፥ ከተማዪቱን ወደ ሸለቆ ስበን እንከታታለን።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሸሽቶ ወደ ከተማም ቢገባ ሕዝባችን በሙሉ ገመድ አምጥተው ከተማይቱን በመሳብ በእርስዋ ሥር ወደሚገኘው ሸለቆ አሽቀንጥረው ይጥሉአታል፤ በኮረብታውም ላይ አንድ ድንጋይ እንኳ አይቀርም።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ከተማም ቢገባ እስራኤል ሁሉ ወደዚያች ከተማ ገመድ ይወስዳል፥ እኛም አንድ ድንጋይ እንኳ እስከማይገኝባት ድረስ ወደ ወንዙ ውስጥ እንስባታለን። |
አቤሴሎምና የእስራኤልም ሰዎች ሁሉ “የአርካዊው የኩሲ ምክር ከአኪጢፌል ምክር ይሻላል” አሉ። እግዚአብሔርም በአቤሴሎም ላይ ክፉ ያመጣ ዘንድ እግዚአብሔር መልካሚቱን የአኪጦፌልን ምክር እንዲበትን አዘዘ።
ስለዚህ ሰማርያን በሜዳ እንደሚገኝ የድንጋይ ክምር፥ ወይን እንደሚተከልበትም ስፍራ አደርጋታለሁ፥ ድንጋዮችዋንም ወደ ሸለቆ እወረውራለሁ፥ መሠረቶችዋንም እገልጣለሁ።