Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 17:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 እር​ሱ​ንም ወደ​ም​ና​ገ​ኝ​በት ወደ አንድ ስፍራ እን​ደ​ር​ስ​በ​ታ​ለን፤ ጠልም በም​ድር ላይ እን​ደ​ሚ​ወ​ድቅ እን​ወ​ር​ድ​በ​ታ​ለን፤ እር​ሱ​ንና ከእ​ር​ሱም ጋር ያሉ ሰዎ​ችን ሁሉ አንድ ስንኳ አና​ስ​ቀ​ርም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ከዚያም እርሱ የገባበት ቦታ ሁሉ ገብተን አደጋ እንጥልበታለን፤ ጤዛ በመሬት ላይ እንደሚወርድ እንወርድበታለን፤ እርሱም ሆነ ሰዎቹ አንድ እንኳ አይተርፉም፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ከዚያም እርሱ ይገኝበታል የተባለው ቦታ ገብተን እናገኝዋለን፥ ጠል መሬት ላይ እንደሚወርድ እንወርድበታለን፤ እርሱም ሆነ ሰዎቹ አንድ እንኳ አይተርፉም፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 የትም ስፍራ ቢደበቅ ዳዊትን ፈልገን እናገኘዋለን፤ በረዶ በምድር ላይ እንደሚወርድ እንወርድበታለን፤ እርሱም ሆነ ከተከታዮቹ አንድ ሰው እንኳ በሕይወት የሚተርፍ አይኖርም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 እርሱንም ወደምናገኝበት ወደ አንድ ስፍራ እንደርስበታለን፥ ጠልም በምድር ላይ እንደሚወድቅ እንወርድበታለን፥ እርሱና ከእርሱም ጋር ያሉ ሰዎች ሁሉ አንድ ስንኳ አናስቀርም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 17:12
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሁለት የሐ​ሰት ምስ​ክ​ሮ​ች​ንም በፊቱ አስ​ቀ​ም​ጡና፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንና ንጉ​ሡን ሰድ​ቦ​አል ብለው ይመ​ስ​ክ​ሩ​በት፤ አው​ጥ​ታ​ች​ሁም እስ​ኪ​ሞት ድረስ በድ​ን​ጋይ መት​ታ​ችሁ ግደ​ሉት።”


አሁ​ንም እን​ግ​ዲህ ከጌ​ታዬ ከአ​ሦር ንጉሥ ጋር ተወ​ራ​ረድ፤ የሚ​ቀ​መ​ጡ​ባ​ቸ​ው​ንም ሰዎች ማግ​ኘት ቢቻ​ልህ እኔ ሁለት ሺህ ፈረ​ሶች እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ።


ዕረ​ፍት አደ​ረ​ግሁ፤ የባ​ዕድ ውኃ​ንም ጠጣሁ፥ የተ​ገ​ደ​በ​ው​ንም ውኃ ሁሉ በእ​ግሬ ጫማ አደ​ር​ቃ​ለሁ።


ሥራው ምስ​ጋ​ናና የጌ​ት​ነት ክብር ነው። ጽድ​ቁም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይኖ​ራል።


በተ​ሰ​ነ​ጠ​ቀም ዓለት ውስጥ እን​ደ​ሚ​ኖር- ማደ​ሪ​ያ​ው​ንም ከፍ ከፍ እን​ደ​ሚ​ያ​ደ​ርግ፥ በል​ቡም፦ ወደ ምድር የሚ​ያ​ወ​ር​ደኝ ማን ነው? እን​ደ​ሚል፥ የል​ብህ ትዕ​ቢት እጅግ አኵ​ር​ቶ​ሃል።


የያዕቆብም ቅሬታ በብዙ አሕዛብ መካከል ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደሚወርድ ጠል፥ በሣር ላይ እንደሚወርድ ካፊያ፥ ሰውንም እንደማይጠብቅ፥ የሰውንም ልጆች ተስፋ እንደማያደርግ ይሆናል።


እን​ግ​ዲህ ዕወቁ፤ ከአ​ያ​ችሁ በኋላ ከእ​ና​ንተ ጋር እን​ሄ​ዳ​ለን፤ በዚ​ያ​ችም ምድር ካለ በይ​ሁዳ አእ​ላፍ ሁሉ እፈ​ት​ሻ​ታ​ለሁ።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች