2 ሳሙኤል 15:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤሴሎምም በማለዳ ተነሥቶ በበሩ ጎዳና ይቆም ነበር፤ አቤሴሎምም ከንጉሥ ለማስፈረድ ጉዳይ የነበረውን ሁሉ ወደ እርሱ እየጠራ፥ “አንተ ከወዴት ከተማ ነህ?” ብሎ ይጠይቅ ነበር። እርሱም፥ “እኔ አገልጋይህ ከእስራኤል ወገን ከአንዲቱ ነኝ” ይለው ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አቤሴሎምም በማለዳ ተነሥቶ ወደ ከተማዪቱ መግቢያ በር በሚወስደው መንገድ ዳር ሆነ ብሎ ይቆም ነበር። ማንኛውም ባለጕዳይ አቤቱታውን ለንጉሡ አቅርቦ ለማስወሰን በሚመጣበት ጊዜ ሁሉ፣ አቤሴሎም ወደ እርሱ እየጠራ፣ “አንተ ከየትኛው ከተማ ነው የመጣኸው?” በማለት ይጠይቀዋል፤ ያም ሰው፣ “አገልጋይህ ከአንዱ የእስራኤል ነገዶች ነው” ብሎ ይመልስለታል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤሴሎምም በማለዳ ተነሥቶ ወደ ከተማዪቱ መግቢያ በር በሚወስደው መንገድ ዳር ይቆም ነበር። ማናቸውም ባለ ጉዳይ አቤቱታውን ለንጉሡ አቅርቦ ለማስወሰን በሚመጣበት ጊዜ ሁሉ፥ አቤሴሎም ወደ እርሱ እየጠራ፥ “አንተ ከየትኛው ከተማ ነው የመጣኸው?” በማለት ይጠይቀዋል፤ ያም ሰው፥ “አገልጋይህ ከእስራኤል ነገዶች ከአንዱ ነው” ብሎ ይመልስለታል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በማለዳ እየተነሣ በመሄድ ወደ ከተማይቱ ቅጽር በር በሚያስገባው መንገድ ዳር ይቆም ነበር፤ ንጉሡ ጉዳዩን እንዲያይለት የሚፈልግ ጠብ ክርክር ያለበት ሰው ሁሉ ወደዚያ ሲመጣ አቤሴሎም ጠርቶ ከወዴት እንደ መጣ ይጠይቀዋል፤ ሰውየው ከየትኛው ነገድ መሆኑን ከነገረው በኋላ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አቤሴሎምም በማለዳ ተነሥቶ በበሩ አደበባይ ይቆም ነበር፥ አቤሴሎምም ከንጉሥ ለማስፈረድ ጉዳይ የነበረውን ሁሉ ወደ እርሱ እየጠራ፦ አንተ ከወዴት ከተማ ነህ? ብሎ ይጠይቅ ነበር። እርሱም፦ እኔ ባሪያህ ከእስራኤል ነገድ ከአንዲቱ ነኝ ብሎ ይመልስ ነበር። |
ንጉሡም ተነሥቶ በበሩ ተቀመጠ፤ ሕዝቡም ሁሉ ንጉሡ በበሩ ተቀምጧል ብለው ተናገሩ፤ ሕዝቡም ሁሉ በበሩ ወደ ንጉሡ ፊት ወጡ። እስራኤልም እያንዳንዱ ወደ ድንኳኑ ሸሽቶ ገብቶ ነበር።
እነርሱም፥ “በዚች ዕለት ለዚህ ሕዝብ ቸርነት ብታደርግላቸው፥ ደስም ብታሰኛቸው፥ መልካም ነገርንም ብትናገራቸው፥ ሁልጊዜ አገልጋዮች ይሆኑልሃል” ብለው ተናገሩት።
ዮቶርም ሙሴ በሕዝቡ ላይ የሚያደርገውን ሁሉ አይቶ እንዲህ አለው፥ “ብቻህን ተቀምጠህ በሕዝቡ የምታደርገው ይህ ምንድን ነው? ሕዝቡ ሁሉ ከጥዋት ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ በዙሪያህ ቆመዋል።”
ነገርም ቢኖራቸው ወደ እኔ ይመጣሉ፤ በዚህና በዚያ ሰውም መካከል እፈርዳለሁ፤ የእግዚአብሔርንም ሥርዐትና ሕግ አስታውቃቸዋለሁ” አለው።
“በደምና በደም መካከል፥ በፍርድና በፍርድ መካከል፥ በመቍሰልና በመቍሰል መካከል፥ በክርክርና በክርክር መካከል በሀገርህ ውስጥ ሰዎች ስለሚከራከሩበት ክርክር የሚሳንህ የፍርድ ነገር ቢኖር፥ አንተ ተነሥተህ ስሙ በዚያ ይጠራ ዘንድ አምላክህ እግዚአብሔር ወደ መረጠው ስፍራ ትወጣለህ፤
ቦዓዝም ወደ ከተማይቱ በር አደባባይ ወጥቶ በዚያ ተቀመጠ። እነሆም፥ ቦዔዝ ስለ እርሱ ይናገር የነበረው የቅርብ ዘመድ ሲያልፍ ቦዔዝ፦ አንተ ቀርበህ በዚህ ተቀመጥ አለው። እርሱም ቀረብ ብሎ ተቀመጠ።