Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 15:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ከዚ​ህም በኋላ አቤ​ሴ​ሎም ሰረ​ገ​ላና ፈረ​ሶች፥ በፊ​ቱም የሚ​ሮጡ አምሳ ሰዎች አዘ​ጋጀ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ከዚህ በኋላ አቤሴሎም ሠረገላና ፈረሶች እንዲሁም ፊት ፊቱ የሚሮጡ ዐምሳ ሰዎች ለራሱ አዘጋጀ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ከዚህ በኋላ አቤሴሎም ሠረገላና ፈረሶች፥ ፊት ፊቱም የሚሮጡ አምሳ ሰዎች አዘጋጀ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ከዚህ በኋላ አቤሴሎም አንድ ሠረገላና ፈረሶች ለራሱ አደራጀ፤ እንዲሁም ኀምሳ ጋሻ ጃግሬዎች እንዲኖሩት አደረገ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ከዚህም በኋላ አቤሴሎም ሰረገላና ፈረሶች፥ በፊቱም የሚሮጡ አምሳ ሰዎች አዘጋጀ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 15:1
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ ከቤ​ትህ ክፉ ነገ​ርን አስ​ነ​ሣ​ብ​ሃ​ለሁ፤ ሚስ​ቶ​ች​ህ​ንም በዐ​ይ​ኖ​ችህ እያ​የህ እወ​ስ​ዳ​ለሁ፤ ለዘ​መ​ድ​ህም እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በዚ​ችም ፀሐይ ፊት ከሚ​ስ​ቶ​ችህ ጋር ይተ​ኛል።


ወደ ንጉ​ሡም ገቡ። ንጉ​ሡም አላ​ቸው፥ “የጌ​ታ​ች​ሁን አገ​ል​ጋ​ዮች ይዛ​ችሁ ሂዱ፥ ልጄ​ንም ሰሎ​ሞ​ንን በበ​ቅ​ሎዬ ላይ አስ​ቀ​ም​ጡት፥ ወደ ግዮ​ንም አው​ር​ዱት፤


የአ​ጊ​ትም ልጅ አዶ​ን​ያስ፥ “ንጉሥ እሆ​ና​ለሁ” ብሎ ተነሣ፤ ሰረ​ገ​ሎ​ች​ንና ፈረ​ሰ​ኞ​ችን በፊ​ቱም የሚ​ሮጡ አምሳ ሰዎ​ችን አዘ​ጋጀ።


ንጉሥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተማ​ም​ኖ​አ​ልና፥ በል​ዑ​ልም ምሕ​ረት አይ​ና​ወ​ጥም።


ትዕቢት ባለበት በዚያ ውርደት አለ፤ የየዋሃን አፍ ግን ጥበብን ይማራል።


ከጥል በፊት ስድብ ይቀድማል፥ ከመውደቅም በፊት ክፋትን ማወቅ።


ክርክርን የሚወድድ በጠብ ደስ ይለዋል።


ለእ​ርሱ ፈረ​ሶ​ችን እን​ዳ​ያ​በዛ፥ ሕዝ​ቡ​ንም ወደ ግብፅ እን​ዳ​ይ​መ​ልስ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፦ በዚ​ያች መን​ገድ መመ​ለ​ስን አት​ድ​ገም ብሎ​አ​ልና።


እን​ዲ​ህም አለ፥ “በእ​ና​ንተ ላይ የሚ​ነ​ግ​ሠው የን​ጉሡ ሥር​ዐት ይህ ነው፤ ወን​ዶች ልጆ​ቻ​ች​ሁን ወስዶ ሰረ​ገላ ነጂ​ዎ​ችና ፈረ​ሰ​ኞች ያደ​ር​ጋ​ቸ​ዋል፤ በሰ​ረ​ገ​ሎ​ችም ፊት ይሮ​ጣሉ፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች