የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




2 ሳሙኤል 14:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ወደ ንጉ​ሡም ገብ​ተሽ እን​ዲህ ያለ​ውን ቃል ንገ​ሪው” አላት፤ ኢዮ​አ​ብም ቃሉን በእ​ር​ስዋ አፍ አደ​ረገ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዚያም ወደ ንጉሡ ሄደሽ እንዲህ በዪው።” ከዚያም ኢዮአብ የምትናገራቸውን ቃላት ነገራት።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከዚያም ወደ ንጉሡ ሂጂ፤ እንዲህም በዪው።” ከዚያም ኢዮአብ መናገር ያለባትን ነገር ነገራት።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከዚያም በኋላ ወደ ንጉሡ ቀርበሽ እኔ የምነግርሽን ንገሪው” አላት፤ ከዚህ በኋላ እርስዋ ልትናገረው የሚገባትን ሁሉ ኢዮአብ ነገራት።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ወደ ንጉሡም ገብተሽ እንዲህ ያለውን ቃል ንገሪው አላት፥ ኢዮአብም ቃሉን በእርስዋ አፍ አደረገ።

ምዕራፉን ተመልከት



2 ሳሙኤል 14:3
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ንጉ​ሡም፥ “በዚህ ሁሉ ነገር የኢ​ዮ​አብ እጅ ከአ​ንቺ ጋር አለን?” አላት። ሴቲ​ቱም ንጉ​ሡን አለ​ችው፥ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ በሕ​ያው ነፍ​ስህ እም​ላ​ለሁ! ጌታዬ ንጉሥ ከተ​ና​ገ​ረው ነገር ሁሉ ወደ ቀኝም ወደ ግራም ሊል የሚ​ችል የለም፤ አገ​ል​ጋ​ይህ ኢዮ​አብ አዝ​ዞ​ኛል፤ ይህ​ንም ቃል ሁሉ በአ​ገ​ል​ጋ​ይህ አፍ አደ​ረ​ገው።


እን​ዲ​ሁም የቴ​ቁ​ሔ​ዪቱ ሴት ወደ ንጉሥ ገብታ በግ​ን​ባ​ርዋ በም​ድር ላይ ወደ​ቀች፤ ሰግ​ዳም “ንጉሥ ሆይ፥ አድ​ነኝ፤ አድ​ነኝ” አለች።


በካ​ሲ​ፍያ ስፍራ ወደ ነበ​ረው ወደ አለ​ቃው ወደ አዶ ላክ​ኋ​ቸው፤ ለአ​ም​ላ​ካ​ችን ቤትም አገ​ል​ጋ​ዮ​ችን ያመ​ጡ​ልን ዘንድ በካ​ሲ​ፍያ ስፍራ ለሚ​ኖ​ሩት ለአ​ዶና ለወ​ን​ድ​ሞቹ ለና​ታ​ኒም የሚ​ነ​ግ​ሩ​አ​ቸ​ውን በአ​ፋ​ቸው አደ​ረ​ግሁ።


አን​ተም ትና​ገ​ረ​ዋ​ለህ፤ ቃሌ​ንም በአፉ ታደ​ር​ገ​ዋ​ለህ፤ እኔ አን​ደ​በ​ት​ህ​ንና አን​ደ​በ​ቱን አረ​ታ​ለሁ፤ የም​ታ​ደ​ር​ጉ​ት​ንም አለ​ብ​ማ​ች​ኋ​ለሁ።


ቃሌን በአ​ፍሽ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ ሰማ​ይን በዘ​ረ​ጋ​ሁ​በ​ትና ምድ​ርን በመ​ሠ​ረ​ት​ሁ​በት በእጄ ጥላ እጋ​ር​ድ​ሻ​ለሁ፤ ጽዮ​ን​ንም አንቺ ሕዝቤ ነሽ እላ​ታ​ለሁ።


“ከእ​ነ​ርሱ ጋር ያለው ቃል ኪዳኔ ይህ ነው” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ “በአ​ንተ ላይ ያለው መን​ፈሴ በአ​ፍ​ህም ውስጥ ያደ​ረ​ግ​ሁት ቃሌ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘለ​ዓ​ለም ድረስ ከአ​ፍህ፥ ከዘ​ር​ህም አፍ፥ ከዘር ዘር​ህም አፍ አይ​ጠ​ፋም፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እጁን ዘር​ግቶ አፌን ዳሰሰ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለኝ፥ “እነሆ፥ ቃሌን በአ​ፍህ ውስጥ አኑ​ሬ​አ​ለሁ፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በበ​ለ​ዓም አፍ ቃልን አኖረ፤ “ወደ ባላቅ ተመ​ለስ፤ እን​ዲ​ህም በል” አለው።


ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው እንደ አንተ ያለ ነቢይ አስ​ነ​ሣ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ቃሌ​ንም በአፉ አኖ​ራ​ለሁ፤ እንደ አዘ​ዝ​ሁ​ትም ይነ​ግ​ራ​ቸ​ዋል፤