ዮሴፍም በፊቱ ሰዎች ሁሉ ቆመው ሳሉ ሊታገሥ አልተቻለውም፥ “ሰዎቹንም ሁሉ ከፊቴ አስወጡልኝ” ብሎ ተናገረ፤ ዮሴፍ ለወንድሞቹ ራሱን በገለጠ ጊዜ በእርሱ ዘንድ የቆመ ማንም አልነበረም።
2 ሳሙኤል 13:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምጣዱንም ወስዳ በፊቱ ገለበጠች፤ እርሱ ግን ይበላ ዘንድ እንቢ አለ። አምኖንም፥ “ሰውን ሁሉ ከእኔ ዘንድ አስወጡ” አለ፤ ሰውም ሁሉ ከእርሱ ዘንድ ወጣ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም መጋገሪያውን አውጥታ እንጀራውን አቀረበችለት፤ እርሱ ግን መብላት አልፈለገም። አምኖንም፣ “ሰውን ሁሉ ከዚህ አስወጡልኝ” አለ፤ ያለውም ሰው ሁሉ ትቶት ወጣ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም መጋገሪያውን አውጥታ እንጀራውን አቀረበችለት፤ እርሱ ግን መብላት አልፈለገም። አምኖንም፥ “ሰውን ሁሉ ከዚህ አስወጡልኝ” አለ፤ ሰውም ሁሉ ትቶት ወጣ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የጋገረችውንም እንጀራ ከምጣዱ አውጥታ እንዲበላ አቀረበችለት፤ እርሱ ግን መመገቡን እምቢ ብሎ “ሰዎቹን ሁሉ አስወጡልኝ” አለ፤ ሁሉም ወጡ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምጣዱንም ወስዳ በፊቱ ገለበጠች እርሱ ግን ይበላ ዘንድ እንቢ አለ። አምኖንም፦ ሰውን ሁሉ ከእኔ ዘንድ አስወጡ አለ፥ ሰውም ሁሉ ከእርሱ ዘንድ ወጣ። |
ዮሴፍም በፊቱ ሰዎች ሁሉ ቆመው ሳሉ ሊታገሥ አልተቻለውም፥ “ሰዎቹንም ሁሉ ከፊቴ አስወጡልኝ” ብሎ ተናገረ፤ ዮሴፍ ለወንድሞቹ ራሱን በገለጠ ጊዜ በእርሱ ዘንድ የቆመ ማንም አልነበረም።
አምኖንም ትዕማርን፥ “በእጅሽ እበላ ዘንድ መብሉን ወደ እልፍኙ አግቢው” አላት፤ ትዕማርም የሠራችውን እንጎቻ ወስዳ ወንድምዋ አምኖን ወዳለበት እልፍኝ አገባችው።
ትዕማርም ወደ ወንድምዋ ወደ አምኖን ቤት ሄደች፤ ተኝቶም ነበር፤ ዱቄትም ወስዳ ለወሰች፤ በፊቱም እንጎቻ አደረገች፤ ጋገረችም።
ዔግሎምም ከገልገል ከጣዖታቱ ቤት ተመለሰ። ናዖድም፥ “ንጉሥ ሆይ፥ ለብቻህ የምነግርህ የምሥጢር ነገር አለኝ” አለ፤ ዔግሎምም ሁሉ ከእርሱ ዘንድ እንዲወጣ አዘዘ፤ በእርሱም ዘንድ የቆሙት ሁሉ ወጡ ።