የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




2 ሳሙኤል 13:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ዳዊ​ትም፥ “ወደ ወን​ድ​ምሽ ወደ አም​ኖን ቤት ሂጂ፤ መብ​ል​ንም አዘ​ጋ​ጂ​ለት” ብሎ ወደ ትዕ​ማር ቤት ላከ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ዳዊትም፣ “ወንድምሽ አምኖን ቤት ሄደሽ ምግብ እንድታዘጋጂለት” በማለት ለትዕማር እንዲነግሯት ወደ ቤተ መንግሥቱ ላከ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከዚያም ዳዊት፥ “ወንድምሽ አምኖን ቤት ሄደሽ ምግብ እንድታዘጋጂለት” የሚል ትእዛዝ ለትዕማር ላከ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ስለዚህም ዳዊት በቤተ መንግሥት ለምትገኘው ለትዕማር “ወደ ወንድምሽ ወደ አምኖን ቤት ሄደሽ ምግብ አዘጋጂለት” የሚል ትእዛዝ ላከ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ዳዊትም፦ መብልን ታዘጋጂለት ዘንድ ወደ ወንድምሽ ወደ አምኖን ቤት ሂጂ ብሎ መልእክተኞችን ወደ ትዕማር ቤት ላከ።

ምዕራፉን ተመልከት



2 ሳሙኤል 13:7
3 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እን​ዲ​ሁም አም​ኖን፥ ታም​ሜ​አ​ለሁ ብሎ ተኛ፤ ንጉ​ሡም ሊያ​የው መጣ፤ አም​ኖ​ንም ንጉ​ሡን፥ “እኅቴ ትዕ​ማር እን​ድ​ት​መ​ጣና እኔ እያ​የሁ ሁለት እን​ጎቻ እን​ድ​ታ​በ​ስ​ል​ልኝ፥ ከእ​ጅ​ዋም እን​ድ​በላ እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ” አለው።


ትዕ​ማ​ርም ወደ ወን​ድ​ምዋ ወደ አም​ኖን ቤት ሄደች፤ ተኝ​ቶም ነበር፤ ዱቄ​ትም ወስዳ ለወ​ሰች፤ በፊ​ቱም እን​ጎቻ አደ​ረ​ገች፤ ጋገ​ረ​ችም።


ዳዊ​ትም በከ​ተ​ማው ለራሱ ቤቶ​ችን ሠራ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ታቦት ስፍራ አዘ​ጋጀ፤ ድን​ኳ​ንም ተከ​ለ​ላት።