“ኦርዮ ወደ ቤቱ አልሄደም” ብለው ለዳዊት ነገሩት፤ ዳዊትም ኦርዮን፥ “አንተ ከመንገድ የመጣህ አይደለህምን? ስለምን ወደ ቤትህ አልወረድህም?” አለው።
2 ሳሙኤል 11:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኦርዮ ግን ከጌታው አገልጋዮች ሁሉ ጋር በንጉሥ ቤት ደጅ ተኛ፤ ወደ ቤቱም አልወረደም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ኦርዮ ከጌታው አገልጋዮች ሁሉ ጋራ በንጉሡ ቤት ቅጽር በር ተኛ እንጂ፣ ወደ ቤቱ አልወረደም ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን ኦርዮ ከጌታው አገልጋዮች ጋር በቤተ መንግሥቱ ቅጽር በር ተኛ እንጂ ወደ ቤቱ አልወረደም ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኦርዮ ግን ወደ ቤቱ ሳይሄድ ከንጉሡ ክብር ዘበኞች ጋር በቤተ መንግሥቱ የቅጽር በር አጠገብ ተኝቶ ዐደረ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኦርዮ ግን ከጌታው ባሪያዎች ሁሉ ጋር በንጉሥ ቤት ደጅ ተኛ፥ ወደ ቤቱም አልወረደም። |
“ኦርዮ ወደ ቤቱ አልሄደም” ብለው ለዳዊት ነገሩት፤ ዳዊትም ኦርዮን፥ “አንተ ከመንገድ የመጣህ አይደለህምን? ስለምን ወደ ቤትህ አልወረድህም?” አለው።
ዳዊትም ጠራው፤ በፊቱም በላና ጠጣ፤ አሰከረውም፤ ነገር ግን በመሸ ጊዜ ወጥቶ ከጌታው አገልጋዮች ጋር በምንጣፉ ላይ ተኛ፤ ወደ ቤቱም አልወረደም።
ንጉሡም ሮብዓም በፋንታው የናስ ጋሾችን ሠራ፤ በፊቱም ለሚሮጡና የንጉሥን ቤት ደጅ ለሚጠብቁ የዘበኞች አለቆች ሰጣቸው።
ከዚህ በኋላ ንጉሡ ዘወትር ወደ እግዚአብሔር ቤት ሲገባ ዘበኞች ይሸከሙአቸው ነበር፤ መልሰውም በዘበኞች ቤት ውስጥ ያኖሩአቸው ነበር።