የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




2 ሳሙኤል 11:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ኦር​ዮም ደርሶ ወደ እርሱ በገባ ጊዜ ዳዊት የኢ​ዮ​አ​ብ​ንና የሕ​ዝ​ቡን ደኅ​ን​ነት፥ ሰል​ፉም እን​ዴት እንደ ሆነ ጠየ​ቀው።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ኦርዮን በመጣ ጊዜም፣ ዳዊት የኢዮአብንና የሰራዊቱን ሁሉ ደኅንነት እንዲሁም ጦርነቱ እንዴት እየተካሄደ እንዳለ ጠየቀው።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ኦርዮን በመጣ ጊዜም፥ ዳዊት የኢዮአብንና የሠራዊቱን ሁሉ ደኅንነት እንዲሁም ጦርነቱ እንዴት እየተካሄደ እንዳለ ጠየቀው።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ኦርዮ በደረሰ ጊዜ ዳዊት “ኢዮአብና ሠራዊቱ ሁሉ እንዴት ናቸው? የጦርነቱስ ሁኔታ እንዴት ነው?” ሲል ጠየቀው፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ኦርዮም ወደ እርሱ በመጣ ጊዜ ዳዊት የኢዮአብንና የሕዝቡን ደኅንነት፥ ሰልፉም እንዴት እንደ ሆነ ጠየቀው።

ምዕራፉን ተመልከት



2 ሳሙኤል 11:7
5 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“እርሱ ደኅና ነውን?” አላ​ቸው። እነ​ር​ሱም፥ “አዎ ደኅና ነው፤ አሁ​ንም ልጁ ራሔል የአ​ባ​ቷን በጎች ይዛ ትመ​ጣ​ለች” አሉት።


እር​ሱም፥ “ሄደህ ወን​ድ​ሞ​ች​ህና በጎቹ ደኅና እንደ ሆኑ እይ፤ ወሬ​አ​ቸ​ው​ንም አም​ጣ​ልኝ” አለው። ወደ ኬብ​ሮ​ንም ቆላ ላከው፤ ወደ ሴኬ​ምም መጣ።


ዳዊ​ትም ወደ ኢዮ​አብ፦ ኬጤ​ያ​ዊ​ውን ኦር​ዮን ወዲህ ላከው ብሎ ላከ። ኢዮ​አ​ብም ኦር​ዮን ወደ ዳዊት ላከው።


ሙሴም አማ​ቱን ሊገ​ናኝ ወጣ፤ እጅ ነሣው፤ ሳመ​ውም፤ እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም ሰላ​ምታ ተሰ​ጣጡ፤ ወደ ድን​ኳ​ኑም ገቡ።


ዳዊ​ትም ዕቃ​ውን በዕቃ ጠባ​ቂው እጅ አኖ​ረው፤ ወደ​ሚ​ዋ​ጉ​በ​ትም ሮጦ ሄደ፤ የወ​ን​ድ​ሞ​ቹ​ንም ደኅ​ን​ነት ጠየቀ።