Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 11:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ዳዊ​ትም ወደ ኢዮ​አብ፦ ኬጤ​ያ​ዊ​ውን ኦር​ዮን ወዲህ ላከው ብሎ ላከ። ኢዮ​አ​ብም ኦር​ዮን ወደ ዳዊት ላከው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ስለዚህም ዳዊት ለኢዮአብ፣ “ኬጢያዊውን ኦርዮን ወደ እኔ ስደደው” ሲል ላከበት፤ ኢዮአብም ወደ ዳዊት ላከው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ስለዚህም ዳዊት ለኢዮአብ፥ “ሒታዊውን ኦርዮንን ወደ እኔ ስደደው” ሲል ላከበት፤ ኢዮአብም ኦርዮንን ወደ ዳዊት ላከው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ከዚህ በኋላ ዳዊት “ሒታዊውን ኦርዮን ወደ እኔ ላከው” ሲል ወደ ኢዮአብ መልእክት ሰደደ፤ ስለዚህም ኢዮአብ ኦርዮን ወደ ዳዊት ላከው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ዳዊትም ወደ ኢዮአብ፦ ኬጢያዊውን አርዮን ስደድልኝ ብሎ ላከ። ኢዮአብም ኦርዮን ወደ ዳዊት ሰደደው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 11:6
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በዚያን ጊዜ “ሰውየውን አላውቀውም፤” ብሎ ራሱን ሊረግምና ሊምል ጀመረ። ወዲያውም ዶሮ ጮኸ።


ዳግመኛም ሲምል “ሰውየውን አላውቀውም፤” ብሎ ካደ።


እርሱ ግን “የምትዪውን አላውቀውም፤” ብሎ በሁሉ ፊት ካደ።


ጌታም አለ፥ “ይህ ሕዝብ በከ​ን​ፈ​ሮቹ ያከ​ብ​ረ​ኛ​ልና፥ ልቡ ግን ከእኔ የራቀ ነውና፥ በከ​ንቱ ያመ​ል​ኩ​ኛል፤ ሰው ሠራሽ ትም​ህ​ር​ትም ያስ​ተ​ም​ራሉ፤


ሳኦ​ልም፥ “በድ​ያ​ለሁ፤ አሁ​ንም በሕ​ዝቤ ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ፊትና በእ​ስ​ራ​ኤል ፊት እባ​ክህ አክ​ብ​ረኝ፤ ለአ​ም​ላ​ክ​ህም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እሰ​ግድ ዘንድ ከእኔ ጋር ተመ​ለስ” አለው።


በእ​ው​ነት ያመ​ጣ​ህ​ልኝ አይ​ደ​ለም፤ አግ​ባ​ብስ በእ​ው​ነት ታመ​ጣ​ልኝ ዘንድ ነበር። በደ​ልህ፤ እን​ግ​ዲህ ዝም በል፤ የወ​ን​ድ​ምህ መመ​ለ​ሻው ወደ አንተ ነው፤ አን​ተም ትሰ​ለ​ጥ​ን​በ​ታ​ለህ።”


ሴቲ​ቱም አረ​ገ​ዘች፤ ወደ ዳዊ​ትም “አር​ግ​ዤ​አ​ለሁ” ብላ ላከ​ች​በት።


ኦር​ዮም ደርሶ ወደ እርሱ በገባ ጊዜ ዳዊት የኢ​ዮ​አ​ብ​ንና የሕ​ዝ​ቡን ደኅ​ን​ነት፥ ሰል​ፉም እን​ዴት እንደ ሆነ ጠየ​ቀው።


ኬጤ​ያ​ዊው ኦርዮ፤ ሁሉም በሁሉ ሠላሳ ሰባት ናቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች