የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




2 ሳሙኤል 1:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ዳዊ​ትም፥ “ነገሩ ምን​ድን ነው? እስኪ ንገ​ረኝ” አለው። እር​ሱም መልሶ፥ “ሕዝቡ ከሰ​ልፉ ሸሽ​ቶ​አል፤ ከሕ​ዝ​ቡም ብዙው ወደቁ፤ ሞቱም፤ ሳኦ​ልና ልጁ ዮና​ታ​ንም ደግሞ ሞተ​ዋል” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ዳዊትም፣ “ምን ነገር ተፈጠረ?” ሲል ጠየቀው። እርሱም፣ “ሰዎቹ ከጦርነቱ ሸሽተዋል፤ ብዙዎቹ ወድቀዋል፤ ሞተዋል፤ ሳኦልና ልጁ ዮናታንም ሞተዋል” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ዳዊትም፥ “እስቲ ምን ነገር እንደተፈጠረ ንገረኝ?” ሲል ጠየቀው። እርሱም “ሰዎቹ ከጦርነቱ ሸሽተዋል፤ ብዙዎቹ ወድቀዋል፤ ሞተዋልም፤ሳኦልና ልጁ ዮናታንም ሞተዋል” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ዳዊትም “እስቲ የሆነውን ሁሉ ንገረኝ” አለው። እርሱም “ሠራዊታችን ከጦር ግንባር ሸሸ፤ ከሰዎቻችንም ብዙዎቹ ሞቱ፤ ሳኦልና ልጁ ዮናታንም ሞተዋል” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ዳዊትም፦ ነገሩ እንደ ምን ሆነ? እስኪ ንገረኝ አለው። እርሱም መልሶ፦ ሕዝቡ ከሰልፉ ሸሽቶአል፥ ከሕዝቡ ብዙው ወደቁ ሞቱም፥ ሳኦልና ልጁም ዮናታን ደግሞ ሞተዋል አለ።

ምዕራፉን ተመልከት



2 ሳሙኤል 1:4
6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዳዊ​ትም፥ “ከወ​ዴት መጣህ?” አለው፤ እር​ሱም፥ “ከእ​ስ​ራ​ኤል ሰፈር አም​ልጬ መጣሁ” አለው።


ዳዊ​ትም ወሬ​ውን ያመ​ጣ​ለ​ትን ጐል​ማሳ፥ “ሳኦ​ልና ልጁ ዮና​ታን እንደ ሞቱ እን​ዴት ዐወ​ቅህ?” አለው።


መል​ካም ወሬ የያዘ መስ​ሎት እነሆ፥ ሳኦል ሞተ ብሎ የነ​ገ​ረ​ኝን የም​ስ​ራቹ ዋጋ እን​ዲ​ሆን ይዤ በሴ​ቄ​ላቅ ገደ​ል​ሁት።


ሰው​ዬ​ው​ንም፥ “አንተ ከወ​ዴት ነህ?” አለው። እር​ሱም፥ “ጦር​ነቱ ከአ​ለ​በት ስፍራ የመ​ጣሁ እኔ ነኝ፥ ዛሬም ከሰ​ልፍ ሸሸሁ” አለ። እር​ሱም፥ “ልጄ ሆይ! ነገ​ሩስ እን​ዴት ሆነ?” አለው።