ተመልሰውም ቃዴስ ወደ ተባለች ወደ ፍርድ ምንጭ መጡ፤ የአማሌቅን አለቆች ሁሉና በአሳሶን ታማር የሚኖሩ አሞራውያንንም ገደሉአቸው።
2 ሳሙኤል 1:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም ወሬውን ያመጣለትን ጐልማሳ፥ “አንተ ከወዴት ነህ?” አለው፤ እርሱም፥ “እኔ የመጻተኛው የአማሌቃዊው ልጅ ነኝ” ብሎ መለሰለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳዊትም ወሬውን ያመጣለትን ወጣት፣ “ከየት ነው የመጣኸው?” ብሎ ጠየቀው። እርሱም፣ “እኔ የአንድ መጻተኛ አማሌቃዊ ልጅ ነኝ” ብሎ መለሰ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳዊትም ወሬውን ያመጣለትን ወጣት፥ “ከየት ነው የመጣኸው?” ብሎ ጠየቀው። እርሱም፥ “እኔ የአንድ መጻተኛ አማሌቃዊ ልጅ ነኝ” ብሎ መለሰ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊትም ወሬውን ይዞ የመጣውን ያንን ወጣት “የየት አገር ሰው ነህ?” ሲል ጠየቀው። እርሱም “በሀገርህ ውስጥ በመጻተኛነት የሚኖር የዐማሌቃዊ ልጅ ነኝ” ሲል መለሰለት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም ወሬኛውን ጕልማሳ፦ አንተ ከወዴት ነህ? አለው፥ እርሱም፦ እኔ የመጻተኛው የአማሌቃዊው ልጅ ነኝ ብሎ መለሰለት። |
ተመልሰውም ቃዴስ ወደ ተባለች ወደ ፍርድ ምንጭ መጡ፤ የአማሌቅን አለቆች ሁሉና በአሳሶን ታማር የሚኖሩ አሞራውያንንም ገደሉአቸው።
ዳዊትም፥ “አንተ የማን ነህ? ከወዴት መጣህ?” አለው። ያም ግብፃዊ ብላቴና፥ “እኔ የአማሌቃዊ ባሪያ ነኝ፤ ከሦስት ቀንም በፊት ታምሜ ነበርና ጌታዬ ጥሎኝ ሄደ።