እግዚአብሔርንም ይፈሩት ነበር፤ ገንዘባቸውንም ለድሆች ይመጸውቱ ነበር፤ አባታቸውም አደራ ያላቸውን ሁሉ ይጠብቁ ነበር፤ ባልቴትዋንና የሙት ልጆችንም በችጋራቸው ጊዜ ያረጋጓቸው ነበር፤ አባትና እናትም ይሆኗቸው ነበር፤ ከሚበድሏቸው ሰዎች እጅ ያስጥሏቸው፥ ካገኛቸው ሁከትና ኀዘንም ሁሉ ያረጋጓቸው ነበር።