ብዙ ገንዘብም ነበረው፤ ወንዶች ባሮችና ሴቶች ባሮች፥ ግመሎችና አህዮችም ነበሩት፤ ጥሩር የሚለብሱ አምስት መቶ ፈረሶችም ነበሩት፤ ኢሎፍላውያንንና አማሌቃውያንን፥ ሶርያውያንንም ፈጽሞ ድል ይነሣቸው ነበር፤ ቀድሞ ጣዖት ሲያመልክ ግን ድል ሲነሡት ኖረ።