በመቃቢስ ሥልጣን በታች ከአሉ ከሞዓብ አሕዛብም ያምኑ ዘንድ ደስ አላቸው፤ አለቃቸው በቀናች መንገድ ይሄድ ነበርና፥ ፍርዱንም ይመለከቱ ነበር፤ ፈቃዱንም ያደርጉ ነበር፤ የአገራቸውን ፍርድና ያገራቸውን ቋንቋ ይንቁ ነበርና የመቃቢስም ሥራ እንደሚቀናና እንደሚሻል ያስተውሉ ነበር።