ይኸን ነገር ከአየና ከሰማ በኋላም በጎ ሥራ መሥራትን አላቃለለም፤ እግዚአብሔር ይቅር ብሎአቸዋልና የእስራኤል ልጆች የሚሠሩትን ቸርነት ሁሉ መሥራት አላቃለለም፤ ትእዛዙንም ሲተላለፉ እግዚአብሔር በሚቀሥፋቸው ጊዜ ያለቅሱና ይጮሁ ነበር፤ ዳግመኛም ይቅር ይላቸው ነበር፤ ሕጉንም ይጠብቁት ነበር።